የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb17 የካቲት ገጽ 4
  • መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎቻችንን በአግባቡ ተጠቀሙባቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎቻችንን በአግባቡ ተጠቀሙባቸው
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2017
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎቻችንን በሚገባ እንጠቀምባቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • የጥያቄ ሣጥን
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ባሉበት ክልል ውስጥ ጽሑፎችን ማበርከት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ጽሑፎቻችንን በአግባቡ ተጠቀሙባቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2017
mwb17 የካቲት ገጽ 4
አንዲት ሴት የይሖዋ ምሥክሮች ከአምላክ የተላከ ምሥራች! የሚለውን ብሮሹር ሲያበረክቱላት እያዳመጠች

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎቻችንን በአግባቡ ተጠቀሙባቸው

ኢየሱስ “በነፃ እንደተቀበላችሁ በነፃ ስጡ” በማለት አስተምሯል። (ማቴ 10:8) ይህን ግልጽ መመሪያ በመከተል መጽሐፍ ቅዱስን ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ጽሑፎቻችንን ለሰዎች የምናበረክተው ያለምንም ክፍያ ነው። (2ቆሮ 2:17) ይሁን እንጂ እነዚህ ጽሑፎች በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኙ ውድ እውነቶችን ይዘዋል። በተጨማሪም ጽሑፎቻችንን ማተምና በዓለም ዙሪያ ወደሚገኙ ጉባኤዎች ማጓጓዝ ከፍተኛ ድካምና ወጪ ይጠይቃል። በመሆኑም መውሰድ ያለብን የሚያስፈልገንን ያህል ብቻ ነው።

በአደባባይ ምሥክርነትም ሆነ በሌላ የአገልግሎት መስክ በምንካፈልበት ወቅት ለሰዎች ጽሑፎችን ስንሰጥ አስተዋዮች መሆን ያስፈልገናል። (ማቴ 7:6) ለአላፊ አግዳሚው በሙሉ ጽሑፎቻችንን ዝም ብለን ከማደል ይልቅ ከሰዎቹ ጋር በመወያየት ፍላጎታቸውን ለማወቅ ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። በዚህ ርዕስ ላይ በሚገኘው ሣጥን ውስጥ ከተጠቀሱት ጥያቄዎች መካከል ቢያንስ ለአንዱ ‘አዎ’ የሚል መልስ መስጠት ትችላለህ? ግለሰቡ ፍላጎት ይኖረው አይኑረው ማወቅ ካልቻልን ትራክት ብንሰጠው የተሻለ ይሆናል። እርግጥ ነው፣ ግለሰቡ መጽሔት ወይም ሌላ ጽሑፍ እንድንሰጠው ከጠየቀን በደስታ እንሰጠዋለን።—ምሳሌ 3:27, 28

ግለሰቡ . . .

  • ስንናገር በትኩረት ያዳምጣል?

  • በውይይቱ ላይ ተሳትፎ ያደርጋል?

  • ጽሑፉን ለማንበብ ተስማምቷል?

  • መዋጮ ማድረግ ይፈልጋል?

  • ከአምላክ ቃል ላይ ለምንነግረው ሐሳብ አድናቆት አለው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ