የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb16 ታኅሣሥ ገጽ 5
  • “እነሆኝ! እኔን ላከኝ!”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “እነሆኝ! እኔን ላከኝ!”
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለይሖዋ ሲሉ መሥዋዕት ከፍለዋል
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • ለአምላክ መንግሥት መሥዋዕትነት ትከፍላላችሁ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • አስፋፊዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ መዛወር
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
  • ይበልጥ እርዳታ ወደሚያስፈልግበት ቦታ ሄደህ ማገልገል ትችላለህ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
mwb16 ታኅሣሥ ገጽ 5

ክርስቲያናዊ ሕይወት

“እነሆኝ! እኔን ላከኝ!”

የዊሊያምስ ቤተሰብ ወደ ሌላ አገር ሄደው ለማገልገል ሲዘጋጁ

ኢሳይያስ ያሳየውን የፈቃደኝነት መንፈስ ልንኮርጅ ይገባል። ኢሳይያስ እምነት እንዳለው ያሳየ ሲሆን ዝርዝር ጉዳዮችን ባያውቅም እንኳ ተልዕኮውን በመቀበል ፈጣን ምላሽ ሰጥቷል። (ኢሳ 6:8) አናንተስ የመንግሥቱ ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ ሄዳችሁ ለማገልገል ስትሉ ሁኔታችሁን ማመቻቸት ትችሉ ይሆን? (መዝ 110:3) እርግጥ ‘ወጪያችሁን ማስላት’ ይኖርባችኋል። (ሉቃስ 14:27, 28) ሆኖም ለስብከቱ ሥራ ስትሉ መሥዋዕት ለመክፈል ፈቃደኛ ሁኑ። (ማቴ 8:20፤ ማር 10:28-30) ይበልጥ እርዳታ ወደሚያስፈልጋቸው ቦታዎች ሄዶ ማገልገል በተባለው ቪዲዮ ላይ ጎላ ተደርጎ እንደተገለጸው በይሖዋ አገልግሎት ስንካፈል የምናገኘው በረከት ከምንከፍለው ከየትኛውም መሥዋዕት ይበልጣል።

ቪዲዮውን ከተመለከታችሁ በኋላ በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • የወንድም ዊሊያምስ ቤተሰብ አባላት ወደ ኢኳዶር ሄደው ለማገልገል ሲሉ ምን መሥዋዕቶችን ከፍለዋል?

  • ቤተሰቡ ሄደው ማገልገል የሚፈልጉበትን ቦታ ሲመርጡ የትኞቹን ነገሮች ግምት ውስጥ አስገብተዋል?

  • ምን በረከቶች አግኝተዋል?

  • የመንግሥቱ ሰባኪዎች ይበልጥ ከሚያስፈልጉበት ቦታ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ማግኘት የምትችሉት ከየት ነው?

በሚቀጥለው ጊዜ የቤተሰብ አምልኮ ስታደርጉ በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • በቤተሰብ ደረጃ አገልግሎታችንን ማስፋት የምንችለው እንዴት ነው? (km 8/11 4-6)

  • የመንግሥቱ ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ ሄደን ማገልገል ባንችል እንኳ ያለንበትን ጉባኤ ይበልጥ መርዳት የምንችለው እንዴት ነው? (w16.03 23-25)

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ