ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
ከአጉረምራሚነት መራቅ ያለብን ለምንድን ነው?
አጉረምራሚነት ይሖዋን ያሳዝነዋል (ዘኁ 11:1፤ w01 6/15 17 አን. 20)
አጉረምራሚነት አንድ ሰው ራስ ወዳድና አድናቆት የጎደለው መሆኑን ያሳያል (ዘኁ 11:4-6፤ w06 7/15 15 አን. 7)
አጉረምራሚነት ሌሎች ተስፋ እንዲቆርጡ ያደርጋል (ዘኁ 11:10-15፤ it-2 719 አን. 4)
እስራኤላውያን በምድረ በዳ ሳሉ በርካታ ችግሮች ቢያጋጥሟቸውም አመስጋኝ የሚሆኑበት ብዙ ምክንያት ነበራቸው። እኛም ስላገኘናቸው ብዙ በረከቶች ማሰባችን አጉረምራሚ ላለመሆን ይረዳናል።