ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
የይሖዋን መመሪያ ለማግኘት ጥረት ማድረጋችሁን አታቋርጡ
እስራኤላውያን በተደጋጋሚ የይሖዋን መመሪያ ጠይቀዋል (መሳ 20:17, 18, 23፤ w11 9/15 32 አን. 2)
በመጨረሻም እስራኤላውያን ይሖዋ ስሙን ከነቀፋ ነፃ ለማድረግ እንዲረዳቸው በእሱ ሙሉ በሙሉ ታመኑ (መሳ 20:26-28)
ያለብን ችግር መፍትሔ ካላገኘ የይሖዋን መመሪያ ለማግኘት ጥረት ማድረጋችንን እና ሙሉ በሙሉ በእሱ መታመናችንን መቀጠል አለብን (መሳ 20:35፤ ሉቃስ 11:9፤ w11 9/15 32 አን. 4)
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ፈተና ሲያጋጥመኝ ወዲያው ወደ ይሖዋ ዘወር እላለሁ? ጥበብና መመሪያ እንዲሰጠኝ ደጋግሜ እጠይቀዋለሁ?’