የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb16 መስከረም ገጽ 8
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስንመራ ማድረግ የሌሉብን ነገሮች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስንመራ ማድረግ የሌሉብን ነገሮች
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምራት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁ ተጠምቀው ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ እርዷቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021
  • በቀላሉ የሚገባ
    ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
  • እውቀት በተባለው መጽሐፍ አማካኝነት ደቀ መዛሙርት ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
mwb16 መስከረም ገጽ 8

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስንመራ ማድረግ የሌሉብን ነገሮች

በወረቀት የሚታተመው
አንድ ወንድም በጥናቱ ወቅት ብዙ ሲያወራ

ብዙ ማውራት፦ ሁሉንም ነገር አንተ ማብራራት እንዳለብህ ሊሰማህ አይገባም። ኢየሱስ ጥያቄዎችን በመጠቀም አድማጮቹ ራሳቸው አስበው ትክክለኛው መደምደሚያ ላይ እንዲደርሱ ረድቷቸዋል። (ማቴ 17:24-27) ጥያቄዎች ውይይቱ አስደሳች እንዲሆን እንዲሁም ተማሪው ትምህርቱ ገብቶትና አምኖበት እንደሆነ ለማወቅ ያስችላሉ። (be 253 አን. 3-4) ጥያቄ ከጠየቅክ በኋላ ተማሪው መልስ እስኪሰጥ ድረስ በትዕግሥት ጠብቀው። የሰጠው መልስ የተሳሳተ ከሆነ ትክክለኛውን መልስ ከመናገር ይልቅ ተጨማሪ ጥያቄዎችን በመጠቀም እሱ ራሱ ትክክለኛው መደምደሚያ ላይ እንዲደርስ እርዳው። (be 238 አን. 1-2) አዳዲስ ሐሳቦችን መናገር ያለብህ ተማሪው ሐሳቡን እንዲረዳው በሚያስችለው ፍጥነት መሆን አለበት።—be 230 አን. 4

የምናረጅበትን ምክንያት በተመለከተ የተወሳሰቡ ዝርዝር ሐሳቦች

ትምህርቱን ማወሳሰብ፦ ስለምትወያዩበት ርዕሰ ጉዳይ የምታውቀውን ነገር ሁሉ ከመናገር ተቆጠብ። (ዮሐ 16:12) በአንቀጹ ዋና ነጥብ ላይ ትኩረት አድርግ። (be 226 አን. 4-5) አንዳንድ ዝርዝር ነጥቦች ትኩረት የሚስቡ ቢሆኑም እንኳ ዋናው ነጥብ እንዲድበሰበስ ሊያደርጉ ይችላሉ። (be 235 አን. 3) ተማሪው ዋናው ነጥብ ግልጽ ከሆነለት ወደ ቀጣዩ አንቀጽ እለፍ።

አንድ ወንድም ብዙ ሐሳቦችን በመናገር ተማሪውን ግራ ሲያጋባው

ምዕራፉን ብቻ ለመሸፈን መጣር፦ ዋናው ዓላማችን ጽሑፉ ላይ ያለውን ሐሳብ መሸፈን ሳይሆን የተማሪውን ልብ መንካት ነው። (ሉቃስ 24:32) በትምህርቱ ውስጥ ያሉትን ቁልፍ ጥቅሶች በሚገባ በማብራራት የአምላክ ቃል ያለውን ኃይል ተጠቀምበት። (2ቆሮ 10:4፤ ዕብ 4:12፤ be 144 አን. 1-3) ቀላል ምሳሌዎችን ተጠቀም። (be 245 አን. 2-4) ተማሪው ያሉበትን ችግሮችና የሚያምንባቸውን ነገሮች ግምት ውስጥ በማስገባት ትምህርቱን ለተማሪው በሚስማማ መንገድ ለማቅረብ ሞክር። እንደሚከተለው ያሉ ጥያቄዎችን ጠይቅ፦ “አሁን ስለተወያየንበት ጉዳይ ምን ይሰማሃል?” “ይህ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረናል?” “ይህን ምክር ተግባራዊ ማድረግ ምን ጥቅም የሚያስገኝ ይመስልሃል?”—be 238 አን. 3-5፤ 259 አን. 1

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ