የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • th ጥናት 14 ገጽ 17
  • ዋና ዋና ነጥቦች ጎላ ብለው እንዲታዩ ማድረግ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ዋና ዋና ነጥቦች ጎላ ብለው እንዲታዩ ማድረግ
  • ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ዋና ዋና ነጥቦች ጎላ ብለው እንዲታዩ ማድረግ
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • አርዕስቱንና ዋና ዋና ነጥቦችን ማጉላት
    ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ
  • አስተዋጽኦ ማዘጋጀት
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • ጭብጡን ማዳበር
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
ለተጨማሪ መረጃ
ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
th ጥናት 14 ገጽ 17

ጥናት 14

ዋና ዋና ነጥቦች ጎላ ብለው እንዲታዩ ማድረግ

ጥቅስ

ዕብራውያን 8:1

ፍሬ ሐሳብ፦ አድማጮችህ ንግግርህን በትኩረት እንዲከታተሉ እርዳቸው፤ በተጨማሪም እያንዳንዱ ዋና ነጥብ ከንግግርህ ዓላማና ጭብጥ ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ግልጽ አድርግላቸው።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • የንግግርህን ዓላማ ለይተህ እወቅ። የንግግሩ ዓላማ መረጃ መስጠት ነው? አንድ ነገር ትክክል መሆን አለመሆኑን ማሳመን ነው? ወይስ አድማጮችህን ለተግባር ማነሳሳት? ይህን ከግምት በማስገባት ንግግርህን አዋቅር። ዋና ዋና ነጥቦቹን የምታብራራበት መንገድ የንግግርህን ዓላማ ለማሳካት የሚያስችል መሆን አለበት።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦ ‘አድማጮቼ ከዚህ ርዕሰ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የትኞቹ ጥያቄዎች ሊፈጠሩባቸው ይችላሉ? ምን ለየት ያለ አመለካከት ሊኖራቸው ይችላል? መልስ ካገኙ በኋላስ ምን ተጨማሪ ጥያቄዎች ሊያነሱ ይችላሉ?’ ከዚያም አድማጮችህ ትምህርቱን በትኩረት ለመከታተል፣ ለመረዳትና አምነው ለመቀበል በሚያስችላቸው መንገድ ነጥቦቹን አደራጅ።

  • የንግግርህን ጭብጥ ጎላ አድርገህ ግለጽ። ንግግርህን ስታቀርብ ከጭብጡ ጋር የተያያዙ ቁልፍ ቃላትን ወይም ሌሎች ተመሳሳይ ቃላትን በተደጋጋሚ ጥቀስ።

  • ዋና ዋናዎቹ ነጥቦች ግልጽና ያልተወሳሰቡ እንዲሆኑ አድርግ። ከጭብጡ ጋር የሚዛመዱትንና በተመደበልህ ጊዜ ውስጥ በደንብ ማብራራት የምትችላቸውን ዋና ዋና ነጥቦች ብቻ ምረጥ። ዋና ዋና ነጥቦችን አታብዛ፤ እያንዳንዱን ዋና ነጥብ በግልጽ ተናገር፤ አንዱን ዋና ነጥብ አብራርተህ ወደ ሌላው ከመሸጋገርህ በፊት ትንሽ ቆም በል፤ የንግግርህ ፍሰት ሳይስተጓጎል ከአንዱ ወደ ሌላው ነጥብ ለመሸጋገር ጥረት አድርግ።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    አድማጮችህ ትምህርቱን በደንብ መከታተል እንዲችሉ ዋና ዋና ነጥቦቹን መግቢያህ ላይ መጥቀስ ትችላለህ፤ ነጥቦቹን እንዲያስታውሷቸው ለመርዳት ደግሞ መደምደሚያህ ላይ ደግመህ ልትጠቅሳቸው ትችላለህ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ