የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
የካቲት 27, 2012 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። እያንዳንዱ ነጥብ ውይይት የሚደረግበት ቀን የተገለጸው በየሳምንቱ ለትምህርት ቤቱ ዝግጅት በምናደርግበት ወቅት ምርምር እንድናደርግ ታስቦ ነው።
1. የይሖዋ ፍትሕ በምሕረቱ ይለዝባል ብሎ መናገር ትክክል ነው? (ኢሳ. 30:18) [ጥር 9, w02 3/1 ገጽ 30]
2. ሳምናስ ከሕዝቅኤል ቤት መጋቢነት ሥራው እንዲወርድ ስለ መደረጉ ከሚገልጸው ዘገባ ምን ትምህርት እናገኛለን? (ኢሳ. 36:2, 3, 22) [ጥር 16, w07 1/15 ገጽ 9 አን. 1]
3. አስጨናቂ ሁኔታዎችን መወጣት የምንችልበትን መንገድ በተመለከተ በኢሳይያስ 37:1, 14-20 ላይ ከሰፈረው ዘገባ ምን ትምህርት እናገኛለን? [ጥር 16, w07 1/15 ገጽ 9 አን. 2-3]
4. በኢሳይያስ 40:31 ላይ የተጠቀሰው ምሳሌ የይሖዋ አገልጋዮችን የሚያበረታታው እንዴት ነው? [ጥር 23, w96 6/15 ገጽ 10-11]
5. በኢሳይያስ 41:14 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው የይሖዋ ቃል በተለይ በዛሬው ጊዜ በጣም አበረታች ነው የምንለው በቅርቡ ምን ዓይነት ጥቃት ስለሚሰነዘር ነው? [ጥር 23, ip-2 ገጽ 24 አን. 16]
6. ‘ጽድቅን እየተከታተልን’ እንደሆነ ለይሖዋ ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? (ኢሳ. 51:1) [የካ. 6, ip-2 ገጽ 165 አን. 2]
7. በኢሳይያስ 53:12 ላይ ‘ታላላቅ’ የተባሉት እነማን ናቸው? ይሖዋ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ያለው ግንኙነት ስለእሱ ምን ነገር እንድንገነዘብ ያስችለናል? [የካ. 13, ip-2 ገጽ 213 አን. 34]
8. በኢሳይያስ 60:17 ላይ በምሳሌያዊ ሁኔታ በተገለጸው መሠረት የይሖዋ ሕዝቦች በመጨረሻዎቹ ቀናት ምን ነገር አግኝተዋል? [የካ. 20, ip-2 ገጽ 316 አን. 22]
9. ኢየሱስና ተከታዮቹ የሚያውጁት ‘የይሖዋ የበጎ ፈቃድ ዓመት’ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (ኢሳ. 61:2 NW) [የካ. 20, ip-2 ገጽ 324 አን. 7-8]
10. በኢሳይያስ 63:9 ላይ ጎላ ተደርጎ የተገለጸው የትኛው የይሖዋ አስደናቂ ባሕርይ ነው? [የካ. 27, w03 7/1 ገጽ 19 አን. 22-23]