-
ዘፍጥረት 48:17-19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 ዮሴፍም አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ እንዳደረገ ሲያይ ቅር ተሰኘ፤ ስለዚህ የአባቱን እጅ ከኤፍሬም ራስ ላይ አንስቶ በምናሴ ራስ ላይ ሊያደርገው ሞከረ። 18 ዮሴፍም አባቱን “አባቴ፣ እንዲህ አይደለም፤ በኩሩ+ እኮ ይሄኛው ነው። ቀኝ እጅህን በእሱ ራስ ላይ አድርግ” አለው። 19 አባቱ ግን “አውቄአለሁ ልጄ፣ አውቄአለሁ። እሱም ቢሆን ሕዝብ ይሆናል፤ ታላቅም ይሆናል። ይሁን እንጂ ታናሽ ወንድሙ ከእሱ የበለጠ ይሆናል፤+ ዘሩም በዝቶ ብዙ ብሔር ለመሆን ይበቃል”+ በማለት እንቢ አለው።
-