ዘፍጥረት 38:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 ይሁን እንጂ ልጁ እጁን በመለሰ ጊዜ ወንድሙ ቀድሞት ወጣ፤ በመሆኑም አዋላጇ “አንተ እንዴት ጥሰህ ወጣህ?” አለች። በመሆኑም ስሙ ፋሬስ*+ ተባለ። ዘኁልቁ 26:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 የይሁዳ ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከሴሎም+ የሴሎማውያን ቤተሰብ፣ ከፋሬስ+ የፋሬሳውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከዛራ+ የዛራውያን ቤተሰብ። ማቴዎስ 1:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ይሁዳ ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን+ ወለደ፤ፋሬስ ኤስሮንን ወለደ፤+ኤስሮን ራምን ወለደ፤+