-
መዝሙር 14:1-7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 ሞኝ* ሰው በልቡ
“ይሖዋ የለም” ይላል።+
ሥራቸው ብልሹ ነው፤ ተግባራቸውም አስጸያፊ ነው፤
መልካም የሚሠራ ማንም የለም።+
2 ሆኖም ጥልቅ ማስተዋል ያለውና ይሖዋን የሚፈልግ ሰው ይኖር እንደሆነ ለማየት፣
ይሖዋ ከሰማይ ሆኖ ወደ ሰው ልጆች ይመለከታል።+
3 ሁሉም መንገድ ስተዋል፤+
ሁሉም ብልሹ ናቸው።
መልካም የሚሠራ ማንም የለም፤
አንድ እንኳ የለም።
4 ከክፉ አድራጊዎቹ መካከል አንዳቸውም አያስተውሉም?
ምግብ እንደሚበሉ ሕዝቤን ይውጣሉ።
ይሖዋን አይጠሩም።
5 ይሁንና በታላቅ ሽብር ይዋጣሉ፤+
ይሖዋ ከጻድቅ ትውልድ ጋር ነውና።
6 እናንተ ክፉ አድራጊዎች የችግረኛውን ሰው ዕቅድ ለማጨናገፍ ትሞክራላችሁ፤
ይሖዋ ግን መጠጊያው ነው።+
7 የእስራኤል መዳን ምነው ከጽዮን በመጣ!+
ይሖዋ የተማረከውን ሕዝቡን በሚመልስበት ጊዜ፣
ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤል ሐሴት ያድርግ።
-
-
ሮም 3:10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 ይህም እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈው ነው፦ “ጻድቅ ሰው የለም፤ አንድም እንኳ የለም፤+
-