የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 53:በመዝሙሩ አናት ላይ የሚገኘው መግለጫ-6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በማሃላት ቅኝት።* ማስኪል።* የዳዊት መዝሙር።

      53 ሞኝ* ሰው በልቡ

      “ይሖዋ የለም” ይላል።+

      የዓመፅ ድርጊታቸው ብልሹና አስጸያፊ ነው፤

      መልካም የሚሠራ ማንም የለም።+

       2 ሆኖም ጥልቅ ማስተዋል ያለውና ይሖዋን የሚፈልግ ሰው ይኖር እንደሆነ ለማየት+

      አምላክ ከሰማይ ሆኖ ወደ ሰው ልጆች ይመለከታል።+

       3 ሁሉም ወደ ሌላ ዞር ብለዋል፤

      ሁሉም ብልሹ ናቸው።

      መልካም የሚሠራ ማንም የለም፤

      አንድ እንኳ የለም።+

       4 ከክፉ አድራጊዎቹ መካከል አንዳቸውም አያስተውሉም?

      ምግብ እንደሚበሉ ሕዝቤን ይውጣሉ።

      ይሖዋን አይጠሩም።+

       5 ይሁንና በታላቅ ሽብር፣

      ከዚህ በፊት ተሰምቷቸው በማያውቅ ታላቅ ፍርሃት ይዋጣሉ፤*

      በአንተ ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩትን* ሰዎች አጥንት አምላክ ይበታትነዋልና።

      ይሖዋ ስላልተቀበላቸው አንተ ታዋርዳቸዋለህ።

       6 የእስራኤል መዳን ምነው ከጽዮን በመጣ!+

      ይሖዋ የተማረከውን ሕዝቡን በሚመልስበት ጊዜ፣

      ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤል ሐሴት ያድርግ።

  • ሮም 3:10-12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 ይህም እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈው ነው፦ “ጻድቅ ሰው የለም፤ አንድም እንኳ የለም፤+ 11 ማስተዋል ያለው አንድም ሰው የለም፤ ደግሞም አምላክን የሚፈልግ አንድም ሰው የለም። 12 ሁሉም መንገድ ስተዋል፤ ሁሉም የማይረቡ ሆነዋል፤ ደግነት የሚያሳይ አንድም ሰው የለም፤ አንድም እንኳ አይገኝም።”+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ