መዝሙር 14:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ሞኝ* ሰው በልቡ “ይሖዋ የለም” ይላል።+ ሥራቸው ብልሹ ነው፤ ተግባራቸውም አስጸያፊ ነው፤መልካም የሚሠራ ማንም የለም።+ 2 ሆኖም ጥልቅ ማስተዋል ያለውና ይሖዋን የሚፈልግ ሰው ይኖር እንደሆነ ለማየት፣ይሖዋ ከሰማይ ሆኖ ወደ ሰው ልጆች ይመለከታል።+ መዝሙር 53:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 53 ሞኝ* ሰው በልቡ “ይሖዋ የለም” ይላል።+ የዓመፅ ድርጊታቸው ብልሹና አስጸያፊ ነው፤መልካም የሚሠራ ማንም የለም።+ ሶፎንያስ 1:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 በዚያ ጊዜ ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ደግሞም ቸልተኛ የሆኑትንና*በልባቸው ‘ይሖዋ መልካምም ሆነ ክፉ ነገር አያደርግም’ የሚሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።+
14 ሞኝ* ሰው በልቡ “ይሖዋ የለም” ይላል።+ ሥራቸው ብልሹ ነው፤ ተግባራቸውም አስጸያፊ ነው፤መልካም የሚሠራ ማንም የለም።+ 2 ሆኖም ጥልቅ ማስተዋል ያለውና ይሖዋን የሚፈልግ ሰው ይኖር እንደሆነ ለማየት፣ይሖዋ ከሰማይ ሆኖ ወደ ሰው ልጆች ይመለከታል።+