-
መዝሙር 64:2, 3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 ከክፉ ሰዎች ስውር ሴራ፣
ከክፉ አድራጊዎች ሸንጎ ጠብቀኝ፤+
3 እነሱ ምላሳቸውን እንደ ሰይፍ ይስላሉ፤
መርዘኛ ቃላቸውን እንደ ቀስት ያነጣጥራሉ፤
-
መዝሙር 121:4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 እነሆ፣ እስራኤልን የሚጠብቀው፣
ፈጽሞ አያንቀላፋም፤ ደግሞም አይተኛም።+
-
-
ኢሳይያስ 54:17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 አንቺን ለማጥቃት የተሠራ ማንኛውም መሣሪያ ይከሽፋል፤+
አንቺን ለመክሰስ የሚነሳን ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ።
-
-
ኢሳይያስ 60:2አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 እነሆ፣ ጨለማ ምድርን፣
ድቅድቅ ጨለማም ብሔራትን ይሸፍናል፤
በአንቺ ላይ ግን ይሖዋ ያበራል፤
ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል።
-
-
-