ዘዳግም 32:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 የሹሩን* ሲወፍር በዓመፀኝነት ተራገጠ። ሰባህ፤ ፈረጠምክ፤ ደለብክ።+ ስለሆነም የሠራውን አምላክ ተወ፤+አዳኝ የሆነለትን ዓለት ናቀ። ዘዳግም 33:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 የሕዝቡ መሪዎች ከመላው የእስራኤል ነገድ ጋር+አንድ ላይ በተሰበሰቡ ጊዜ፣+አምላክ በየሹሩን*+ ላይ ንጉሥ ሆነ። ዘዳግም 33:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 አንተን ለመርዳት በሰማይ ውስጥ የሚጋልብ፣በግርማው በደመና ላይ የሚገሰግስ፣+እንደ እውነተኛው የየሹሩን+ አምላክ ያለ ማንም የለም።+