የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘሌዋውያን 18:24
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 24 “‘ከእነዚህ ነገሮች በየትኛውም ራሳችሁን አታርክሱ፤ ምክንያቱም ከእናንተ ፊት አባርሬ የማስወጣቸው ብሔራት ራሳቸውን በእነዚህ ነገሮች አርክሰዋል።+

  • ዘኁልቁ 35:33, 34
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 33 “‘ደም ምድሪቱን ስለሚበክል ያላችሁባትን ምድር አትበክሉ፤+ ደም ባፈሰሰው ሰው ደም ካልሆነ በስተቀር በምድሪቱ ላይ ለፈሰሰው ደም ስርየት ሊኖር አይችልም።+ 34 የምትኖሩባትን፣ እኔም የምኖርባትን ምድር አታርክሱ፤ እኔ ይሖዋ በእስራኤል ሕዝብ መካከል እኖራለሁና።’”+

  • 2 ዜና መዋዕል 33:9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 ምናሴም ይሖዋ ከእስራኤላውያን ፊት ካጠፋቸው ብሔራት የባሰ ክፉ ነገር እንዲሠሩ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች አሳተ።+

  • ኤርምያስ 3:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 ሰዎች እንዲህ ብለው ይጠይቃሉ፦ “አንድ ሰው ሚስቱን ቢያሰናብታት፣ እሷም ተለይታው ብትሄድና የሌላ ሰው ሚስት ብትሆን፣ ዳግመኛ ወደ እሷ መመለስ ይኖርበታል?”

      ይህች ምድር ጨርሶ ተበክላ የለም?+

      “አንቺ ከብዙ ወዳጆችሽ ጋር አመነዘርሽ፤+

      ታዲያ አሁን ወደ እኔ መመለስ ይገባሻል?” ይላል ይሖዋ።

  • ኤርምያስ 23:10, 11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 ምድሪቱ በአመንዝሮች ተሞልታለችና፤+

      ከእርግማኑ የተነሳ ምድሪቱ አዝናለች፤+

      በምድረ በዳ ያሉት ማሰማሪያዎችም ደርቀዋል።+

      መንገዳቸው መጥፎ ነው፤ ሥልጣናቸውንም አላግባብ ይጠቀሙበታል።

      11 “ነቢዩም ሆነ ካህኑ ተበክለዋል።*+

      በገዛ ቤቴ እንኳ ሳይቀር የሠሩትን ክፋት አግኝቻለሁ”+ ይላል ይሖዋ።

  • ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ይህ የደረሰው ነቢያቷ በሠሩት ኃጢአትና ካህናቷ በፈጸሙት በደል የተነሳ ነው፤+

      እነሱ በመካከሏ የነበሩትን ጻድቃን ደም አፍስሰዋል።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ