የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 14:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 በዚህ ጊዜ እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! እነሆ፣ ነቢያቱ ‘ሰይፍ አታዩም፤ ለረሃብም አትዳረጉም፤ ከዚህ ይልቅ በዚህ ስፍራ እውነተኛ ሰላም እሰጣችኋለሁ’ ይሏቸዋል።”+

  • ኤርምያስ 23:16, 17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

      “ትንቢት የሚተነብዩላችሁ ነቢያት የሚናገሩትን ቃል አትስሙ።+

      እነሱ እያሞኟችሁ ነው።*

      የሚናገሩት ራእይ ከይሖዋ አፍ የወጣ ሳይሆን+

      ከገዛ ልባቸው የመነጨ ነው።+

      17 እነሱ እኔን ለሚንቁ ሰዎች ደግመው ደጋግመው

      ‘ይሖዋ “ሰላም ታገኛላችሁ” ብሏል’ ይላሉ።+

      ግትር የሆነ ልባቸውን የሚከተሉትን ሁሉ

      ‘ጥፋት አይደርስባችሁም’ ይሏቸዋል።+

  • ኤርምያስ 27:14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ‘የባቢሎንን ንጉሥ አታገለግሉም’ የሚሏችሁን ነቢያት ቃል አትስሙ፤+ ምክንያቱም የሚተነብዩላችሁ ነገር ሐሰት ነው።+

  • ኤርምያስ 28:1, 2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 28 በዚያው ዓመት፣ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ+ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ፣ በአራተኛው ዓመት፣ በአምስተኛው ወር፣ የገባኦን+ ሰው የሆነው የአዙር ልጅ ነቢዩ ሃናንያህ፣ በይሖዋ ቤት ውስጥ በካህናቱና በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ አለኝ፦ 2 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁ።+

  • ሰቆቃወ ኤርምያስ 2:14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ነቢያትሽ ያዩልሽ ራእይ ሐሰትና ከንቱ ነው፤+

      ተማርከሽ እንዳትወሰጂ ለማድረግ በደልሽን አላጋለጡም፤+

      ይልቁንም ራእይ ተገለጠልን እያሉ ሐሰትና አሳሳች ቃል ይነግሩሻል።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ