-
ማርቆስ 9:43-48አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
43 “እጅህ ቢያሰናክልህ ቁረጠው። ሁለት እጅ ኖሮህ እሳቱ ሊጠፋ ወደማይችልበት ወደ ገሃነም* ከምትሄድ ጉንድሽ ሆነህ ሕይወት ብታገኝ ይሻልሃል።+ 44 *—— 45 እግርህም ቢያሰናክልህ ቁረጠው። ሁለት እግር ኖሮህ ወደ ገሃነም* ከምትጣል አንካሳ ሆነህ ሕይወት ብታገኝ ይሻልሃል።+ 46 *—— 47 ዓይንህም ቢያሰናክልህ አውጥተህ ጣለው።+ ሁለት ዓይን ኖሮህ ወደ ገሃነም* ከምትጣል አንድ ዓይን ኖሮህ ወደ አምላክ መንግሥት ብትገባ ይሻልሃል፤+ 48 በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱም አይጠፋም።+
-