ኢሳይያስ
16 ከሴላ በምድረ በዳው በኩል አድርጋችሁ
በጽዮን ሴት ልጅ ተራራ ለሚገኘው
ለምድሪቱ ገዢ አውራ በግ ላኩ።
3 “ምክር ለግሱ፤ ውሳኔውን ተግባራዊ አድርጉ።
እኩለ ቀን ላይ እንደ ምሽት ጨለማ ያለ ጥላ አጥሉ።
የተበተኑትን ሸሽጉ፤ የሚሸሹትንም አሳልፋችሁ አትስጡ።
4 ሞዓብ ሆይ፣ የተበተኑት ሕዝቦቼ በአንተ ውስጥ ይኑሩ።
ከአጥፊው+ የተነሳ መሸሸጊያ ቦታ ሁንላቸው።
ጨቋኙ ፍጻሜው ይመጣል፤
ጥፋቱም ያበቃል፤
ሌሎችን የሚረግጡትም ከምድር ገጽ ይጠፋሉ።
5 ከዚያም ዙፋን በታማኝ ፍቅር ጸንቶ ይመሠረታል።
7 በመሆኑም ሞዓብ፣ ስለ ሞዓብ ዋይ ዋይ ይላል፤
አዎ፣ ሁሉም ዋይ ዋይ ይላሉ።+
የተመቱት ሰዎች ስለ ቂርሃረሰት+ የዘቢብ ቂጣ ያለቅሳሉ።
8 በሃሽቦን+ እርከኖች ላይ የሚገኙት ተክሎች ጠውልገዋልና፤
የሲብማ+ የወይን ተክሎች ረግፈዋል፤
የብሔራት ገዢዎች ቀያይ ቅርንጫፎቹን* ረጋግጠዋል፤
እስከ ያዜር+ ደርሰዋል፤
በምድረ በዳውም ተንሰራፍተዋል።
ቀንበጦቹም ተዘርግተው እስከ ባሕሩ ድረስ ዘልቀዋል።
9 ስለዚህ ስለ ያዜር እንዳለቀስኩት ለሲብማ የወይን ተክልም አለቅሳለሁ።
10 ሐሴትና ደስታ ከፍራፍሬ እርሻው ተወስዷል፤
በወይን እርሻዎቹም የደስታ ዝማሬ ወይም ጩኸት አይሰማም።+
ወይን የሚረግጥ ሰው ከእንግዲህ በወይን መጭመቂያው ውስጥ ወይን አይረግጥም፤
ጩኸቱን ሁሉ ጸጥ አሰኝቻለሁና።+
12 ሞዓብ በከፍታ ስፍራው ላይ ራሱን ቢያደክምም እንኳ ዋጋ የለውም፤ ለመጸለይ ወደ መቅደሱ ቢመጣም ምንም ማድረግ አይችልም።+
13 ይሖዋ አስቀድሞ ስለ ሞዓብ የተናገረው ቃል ይህ ነው። 14 ደግሞም ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ልክ እንደ ቅጥር ሠራተኛ የሥራ ዘመን፣* በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የሞዓብ ክብር በብዙ ብጥብጥ ይዋረዳል፤ የሚተርፉትም በጣም ጥቂትና እዚህ ግቡ የማይባሉ ይሆናሉ።”+