ኢሳይያስ
17 በደማስቆ ላይ የተላለፈ ፍርድ፦+
“እነሆ፣ ደማስቆ ከተማ መሆኗ ይቀራል፤
የፍርስራሽ ክምርም ትሆናለች።+
3 የተመሸጉ ከተሞች ከኤፍሬም፣+
መንግሥትም ከደማስቆ ይወገዳል፤+
የተረፉት የሶርያ ሰዎች ክብርም
ልክ እንደ እስራኤላውያን ክብር ይጠፋል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።
4 “በዚያን ቀን የያዕቆብ ክብር ይከስማል፤
ጤናማ የሆነው ሰውነቱም* ይከሳል።
5 አጫጁ በማሳ ውስጥ ያለውን እህል በሚሰበስብበትና
በእጁ ዛላውን በሚቆርጥበት ጊዜ እንደሚሆነው፣
6 የወይራ ዛፍ ሲመታ
ከፍ ባለው ቅርንጫፍ ላይ ሁለት ወይም ሦስት የወይራ ፍሬዎች ብቻ፣
ፍሬ በሚይዙት ቅርንጫፎችም ላይ አራት ወይም አምስት ፍሬዎች ብቻ እንደሚቀሩ፣
በእሱም ላይ ቃርሚያ ብቻ ይቀራል”+ ይላል የእስራኤል አምላክ ይሖዋ።
7 በዚያም ቀን ሰው ወደ ሠሪው ይመለከታል፤ ዓይኖቹም የእስራኤልን ቅዱስ ትኩር ብለው ያያሉ። 8 የእጁ ሥራ+ ወደሆኑት መሠዊያዎች አይመለከትም፤+ ጣቶቹ የሠሯቸውን የማምለኪያ ግንዶችም* ሆነ የዕጣን ማጨሻዎች አተኩሮ አያይም።
ያማሩ ተክሎችን ያለማሽውና
በመካከሉም የባዕድ* ቡቃያ የተከልሽው ለዚህ ነው።
12 አዳምጡ! እንደሚናወጥ ባሕር ያለ
የብዙ ሕዝቦች ትርምስ ይሰማል!
እንደ ኃይለኛ ውኃዎች ድምፅ ያለ
የሚያስገመግም የብሔራት ጫጫታ ይሰማል!
13 ብሔራት እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅ ያለ የሚያስገመግም ድምፅ ያሰማሉ።
እሱ ይገሥጻቸዋል፤ እነሱም ወደ ሩቅ ቦታ ይሸሻሉ፤
በተራራ ላይ እንዳለ በነፋስ እንደሚበን ገለባና
አውሎ ነፋስ እያሽከረከረ እንደሚወስደው ኮሸሽላ ይሆናሉ።
14 ሲመሽ ሽብር ይነግሣል።
ከመንጋቱም በፊት በዚያ አንዳቸውም አይገኙም።
የዘረፉን ሰዎች ድርሻ፣
የበዘበዙንም ሰዎች ዕጣ ይህ ነው።