ምሳሌ
25 እነዚህም የይሁዳ ንጉሥ የሕዝቅያስ+ ሰዎች የጻፏቸው* የሰለሞን ምሳሌዎች ናቸው፦+
2 አንድን ጉዳይ መሰወር ለአምላክ ክብሩ ነው፤+
ጉዳይን በሚገባ መመርመር ደግሞ ለነገሥታት ክብራቸው ነው።
3 ሰማያት ከፍ ያሉ እንደሆኑ፣ ምድርም ጥልቅ እንደሆነች ሁሉ
የንጉሥም ልብ አይመረመርም።
4 የብርን ቆሻሻ አስወግድ፤
ሙሉ በሙሉም የጠራ ይሆናል።+
5 ክፉን ሰው ከንጉሥ ፊት አስወግድ፤
ዙፋኑም በጽድቅ ይጸናል።+
እሱ ራሱ “ወደዚህ ከፍ በል” ቢልህ ይሻላልና።+
8 ክስ ለመመሥረት አትቸኩል፤
የኋላ ኋላ ባልንጀራህ ቢያዋርድህ ምን ይውጥሃል?+
9 ከባልንጀራህ ጋር ስለ ራስህ ጉዳይ ተሟገት፤+
ሆኖም በሚስጥር የተነገረህን ጉዳይ* አትግለጥ፤+
10 አለዚያ የሚሰማህ ሰው ያዋርድሃል፤
ያናፈስከውንም መጥፎ ወሬ* መመለስ አትችልም።
12 በጥበብ ወቀሳ የሚሰጥ ሰው፣ የሚሰማ ጆሮ ላለው
እንደ ወርቅ ጉትቻና ከጥሩ ወርቅ እንደተሠራ ጌጥ ነው።+
16 ማር ካገኘህ የሚበቃህን ያህል ብቻ ብላ፤
ከልክ በላይ ከበላህ ሊያስመልስህ ይችላልና።+
17 እንዳይሰለችህና እንዳይጠላህ
ወደ ባልንጀራህ ቤት እግር አታብዛ።
18 በባልንጀራው ላይ በሐሰት የሚመሠክር
እንደ ቆመጥ፣ እንደ ሰይፍና እንደ ሹል ፍላጻ ነው።+
19 በችግር ወቅት እምነት በማይጣልበት* ሰው መተማመን፣
እንደተሰበረ ጥርስና እንደሰለለ እግር ነው።
23 የሰሜን ነፋስ ኃይለኛ ዝናብ ያመጣል፤
ሐሜተኛ ምላስም የሰውን ፊት ያስቆጣል።+
26 ለክፉ ሰው የሚንበረከክ* ጻድቅ፣
እንደጨቀየ ምንጭና እንደተበከለ የውኃ ጉድጓድ ነው።