ኢሳይያስ
9 ይሁን እንጂ ፅልማሞቱ ምድሪቱ በተጨነቀችበት ጊዜ እንደነበረው ይኸውም የዛብሎን ምድርና የንፍታሌም ምድር በተዋረዱበት ወቅት እንደነበረው እንደቀድሞው ዘመን አይሆንም።+ በኋለኛው ዘመን ግን ምድሩ ማለትም በባሕሩ አጠገብ የሚያልፈው መንገድ፣ በዮርዳኖስ ክልል የሚገኘው የአሕዛብ ገሊላ እንዲከበር ያደርጋል።
2 በጨለማ ውስጥ ይሄዱ የነበሩ ሰዎች
ታላቅ ብርሃን አዩ።
ድቅድቅ ጨለማ ባጠላበት ምድር የሚኖሩ ሰዎችም
ብርሃን ወጣላቸው።+
3 ሕዝቡን አብዝተሃል፤
ታላቅ ደስታ እንዲያገኝ አድርገሃል።
መከር በሚሰበሰብበት ጊዜ ሐሴት እንደሚያደርጉ፣
ምርኮንም ሲከፋፈሉ እንደሚደሰቱ ሰዎች
በፊትህ ደስ ይሰኛሉ።
5 መሬቱ እስኪንቀጠቀጥ ድረስ በኃይል የሚረግጡ ሰልፈኞች ጫማ ሁሉ
እንዲሁም በደም የተጨማለቀ ልብስ በሙሉ
ለእሳት ማገዶ ይሆናል።
ስሙ ድንቅ መካሪ፣+ ኃያል አምላክ፣+ የዘላለም አባትና የሰላም መስፍን ይባላል።
የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቅንዓት ይህን ያደርጋል።
8 ይሖዋ በያዕቆብ ላይ ቃል ላከ፤
ቃሉም በእስራኤል ላይ ደረሰ።+
9 ሕዝቡም ሁሉ ይኸውም የኤፍሬምና የሰማርያ ነዋሪዎች
ይህን ያውቃሉ፤
በትዕቢታቸውና በልባቸው እብሪት የተነሳ እንዲህ ይላሉ፦
10 “ጡቦቹ ወድቀዋል፤
እኛ ግን በጥርብ ድንጋይ እንገነባለን።+
የሾላ ዛፎቹ ተቆርጠዋል፤
እኛ ግን በአርዘ ሊባኖስ እንተካቸዋለን።”
11 ይሖዋ የረጺንን ባላጋራዎች በእሱ ላይ ያስነሳል፤
ጠላቶቹንም እርምጃ እንዲወስዱ ይቀሰቅሳቸዋል፤
12 ሶርያን ከምሥራቅ፣ ፍልስጤማውያንን ደግሞ ከምዕራብ* ያመጣበታል፤+
እነሱም አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይውጡታል።+
ከዚህ ሁሉ የተነሳ ቁጣው አልተመለሰም፤
ይልቁንም እጁ ለመምታት ገና እንደተዘረጋ ነው።+
13 ሕዝቡ ወደመታቸው አልተመለሱምና፤
የሠራዊት ጌታ ይሖዋን አልፈለጉም።+
15 ሽማግሌውና የተከበረው ሰው ራስ ነው፤
የሐሰት መመሪያ የሚሰጠው ነቢይ ደግሞ ጅራት ነው።+
16 ይህን ሕዝብ የሚመሩት ሰዎች እንዲባዝን ያደርጉታል፤
በእነሱ የሚመራውም ሕዝብ ግራ ይጋባል።
17 ይሖዋ በወጣቶቻቸው የማይደሰተው ለዚህ ነው፤
በመካከላቸው ላሉት አባት የሌላቸው ልጆችና* መበለቶች ምሕረት አያሳይም፤
ምክንያቱም ሁሉም ከሃዲዎችና ክፉ አድራጊዎች ናቸው፤+
የሁሉም አፍ የማይረባ ነገር ይናገራል።
ከዚህ ሁሉ የተነሳ ቁጣው አልተመለሰም፤
ይልቁንም እጁ ለመምታት ገና እንደተዘረጋ ነው።+
18 ክፋት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤
ቁጥቋጦውንና አረሙንም ይበላል።
በደን ውስጥ ያለውን ጥሻ ያነደዋል፤
ጥሻው በሚቃጠልበት ጊዜም ጭሱ እየተትጎለጎለ ይወጣል።
19 ከሠራዊት ጌታ ከይሖዋ ቁጣ የተነሳ
ምድሪቷ በእሳት ተያያዘች፤
ሕዝቡም እሳት እንደሚበላው ማገዶ ይሆናል።
ማንም ሰው ወንድሙን እንኳ አይምርም።
20 አንዱ በቀኝ በኩል ይቆርጣል፤
ሆኖም ይራባል፤
ሌላው ደግሞ በግራ በኩል ይበላል፤
ሆኖም አይጠግብም።
እያንዳንዳቸው የገዛ ክንዳቸውን ሥጋ ይበላሉ፤
21 ምናሴ ኤፍሬምን፣
ኤፍሬም ደግሞ ምናሴን ይበላል።
በይሁዳም ላይ በአንድነት ይነሳሉ።+
ከዚህ ሁሉ የተነሳ ቁጣው አልተመለሰም፤
ይልቁንም እጁ ለመምታት ገና እንደተዘረጋ ነው።+