የርዕስ ማውጫ
ጥቅምት 15, 2014
© 2014 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
የጥናት እትም
ከታኅሣሥ 1-7, 2014
ገጽ 7 • መዝሙሮች፦ 14, 54
ከታኅሣሥ 8-14, 2014
ገጽ 13 • መዝሙሮች፦ 44, 28
ከታኅሣሥ 15-21, 2014
ከይሖዋ ጋር የመሥራት መብታችሁን ከፍ አድርጋችሁ ተመልከቱ!
ከታኅሣሥ 22-28, 2014
‘አእምሯችሁ ምንጊዜም በላይ ባሉት ነገሮች ላይ እንዲያተኩር አድርጉ’
ገጽ 28 • መዝሙሮች፦ 42, 22
የጥናት ርዕሶች
▪ በመንግሥቱ ላይ የማይናወጥ እምነት ይኑራችሁ
▪ “የመንግሥት ካህናት” ትሆናላችሁ
ይሖዋ ለምድርና ለሰው ዘር ያለውን ዓላማ ለመፈጸም የሚጠቀምበት መሣሪያ መሲሐዊው መንግሥት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት የተለያዩ ቃል ኪዳኖች በሰማይ ከሚገኘው ከዚህ መንግሥት ጋር የሚያያዙት እንዴት እንደሆነ ስንመረምር በመንግሥቱ ላይ የማይናወጥ እምነት ማዳበር የምንችለው ለምን እንደሆነ ለመረዳት ሞክሩ።
▪ ከይሖዋ ጋር የመሥራት መብታችሁን ከፍ አድርጋችሁ ተመልከቱ!
ይህ ርዕስ በጥንት ዘመንም ሆነ በዛሬው ጊዜ ይሖዋን በታማኝነት ያገለገሉ ሰዎችን ምሳሌ ይዟል። ይህን ርዕስ ማጥናታችን ከአምላካችን ጋር የመሥራት መብታችንን ከፍ አድርገን እንድንመለከት ይረዳናል፤ በእርግጥም ይህ ውድ መብት ነው።
▪ ‘አእምሯችሁ ምንጊዜም በላይ ባሉት ነገሮች ላይ እንዲያተኩር አድርጉ’
በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት በርካታ የእምነት ፈተናዎች ያጋጥሙናል። እንደ አብርሃምና ሙሴ ካሉ በጥንት ጊዜ የኖሩና ተመሳሳይ ፈተና ካጋጠማቸው ታማኝ ሰዎች ምን እንማራለን? ይህ ርዕስ አእምሯችን ምንጊዜም በይሖዋ አምላክና በመንግሥቱ ላይ እንዲያተኩር በማበረታታት መጽናት እንድንችል ይረዳናል።
ሽፋኑ፦ ሁለት እህቶች በእምቦሎሎ ተራሮች አቅራቢያ በደቡብ ምሥራቅ ኬንያ፣ በታይታ አውራጃ የምትገኘውን ታዉሳን አቋርጦ በሚያልፈው ዋና መንገድ ላይ ለሰዎች ሲመሠክሩ
ኬንያ
የሕዝብ ብዛት
44,250,000
አስፋፊዎች
26,060
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
43,034
የ2013 የመታሰቢያው በዓል ተሰብሳቢዎች
60,166