የርዕስ ማውጫ
ሰኔ 15, 2015
© 2015 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
የጥናት ርዕሶች
ከሐምሌ 27, 2015–ነሐሴ 2, 2015
ገጽ 3 • መዝሙሮች፦ 14, 109
ከነሐሴ 3-9, 2015
ገጽ 8 • መዝሙሮች፦ 84, 99
ከነሐሴ 10-16, 2015
ገጽ 13 • መዝሙሮች፦ 83, 57
ከነሐሴ 17-23, 2015
ገጽ 20 • መዝሙሮች፦ 138 ስምህ ይሖዋ ነው (አዲስ መዝሙር), 89
ከነሐሴ 24-30, 2015
ገጽ 25 • መዝሙሮች፦ 22, 68
የጥናት ርዕሶች
▪ ክርስቶስ—የአምላክ ኃይል
▪ የሰው ልጆችን ይወዳል
ኢየሱስ ስለፈጸማቸው ተአምራት የሚያወሱት እነዚህ ርዕሶች ልግስና ስለ ማሳየትና ሌሎችን ስለ መርዳት ጠቃሚ ትምህርት ይሰጡናል፤ እንዲሁም ስለ ኢየሱስ ባሕርያት አስደናቂ ነገር ያስተምሩናል። እነዚህ ርዕሶች በቅርቡ በመላው ምድር ላይ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ተአምራት እንደሚከናወኑ ይገልጻሉ።
▪ ንጽሕናችንን ጠብቀን መኖር እንችላለን
በዓለም ላይ የሚታየው የሥነ ምግባር ሁኔታ ሥነ ምግባራዊ ንጽሕናን ጠብቆ መኖር ተፈታታኝ እንዲሆን አድርጓል። ከይሖዋ ጋር ያለን ዝምድና፣ ከቃሉ የምናገኘው ምክርና የጎለመሱ ክርስቲያኖች የሚሰጡን እርዳታ ርኩስ የሆኑ ሐሳቦችን ለማስወገድና የይሖዋን የላቁ የሥነ ምግባር መሥፈርቶች ለመጠበቅ እንዴት እንደሚረዱን በዚህ ርዕስ ላይ ላይ እንመለከታለን።
▪ ከጸሎት ናሙናው ጋር ተስማምቶ መኖር—ክፍል 1
▪ ከጸሎት ናሙናው ጋር ተስማምቶ መኖር—ክፍል 2
ክርስቲያኖች ኢየሱስ ያስተማረውን የጸሎት ናሙና በየዕለቱ ባይደግሙም በናሙናው ላይ የተገለጹት ልመናዎች ለሁላችንም ትርጉም አላቸው። እነዚህ የጥናት ርዕሶች በጸሎቱ ላይ ከተጠቀሱት ልመናዎች ጋር በሚስማማ መንገድ መኖር የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራሉ።
ሽፋኑ፦ በፓናማ ሰሜናዊ ምዕራብ ዳርቻ አቅራቢያ ባሉት ቦካስ ዴል ቶሮ የሚባሉ ደሴቶች ለሚኖሩ ሰዎች ምሥራቹን ለማድረስ የይሖዋ ምሥክሮች በጀልባዎች ይጠቀማሉ። የሚያከናውኑት ሥራ በንጋቤሬ ቋንቋ ምሥክርነት መስጠትንም ይጨምራል
ፓናማ
የሕዝብ ብዛት
3,931,000
አስፋፊዎች
16,217
የዘወትር አቅኚዎች
2,534
በፓናማ በሚገኙት 309 ጉባኤዎች ውስጥ ከ180 በላይ ልዩ አቅኚዎች አሉ። በንጋቤሬ ቋንቋ በሚመሩ 35 ጉባኤዎችና 15 ቡድኖች ውስጥ 1,100 ያህል አስፋፊዎች ያገለግላሉ። በፓናማ የምልክት ቋንቋ በሚካሄዱት 16 ጉባኤዎችና 6 ቡድኖች ውስጥ ደግሞ 600 ገደማ የሚሆኑ አስፋፊዎች አሉ