የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ማስታወሻ፦ ከዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ጀምሮ የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራሙ በሚቀጥለው ወር የመጀመሪያ ሳምንት ላይ የሚቀርበውን የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም ይዞ ይወጣል። ይህ ማሻሻያ የተደረገው በጽሑፍ መላኪያው አሠራር የተነሳ የመንግሥት አገልግሎታችን ዘግይቶ ቢደርስ የሚባክነውን ጊዜ ለማካካስ ተብሎ ነው።
ታኅሣሥ 6 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 91 (207)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ “የማያዳላውን አምላክ ይሖዋን ምሰሉት።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ ክፍሉን በጥያቄና መልስ አቅርበው። አለማዳላት ምን ትርጉም እንዳለው፣ ይሖዋ ይህን ባሕርይ እንዴት እንደሚያሳይና እኛም በአገልግሎታችን ይህን እንዴት ማሳየት እንደምንችል ግለጽ።—ጠለቅ ብሎ ማስተዋል (እንግሊዝኛ)፣ ጥራዝ 1 ገጽ 1192 አንቀጽ 4-7ን ተመልከት።
20 ደቂቃ፦ “ይህን ነገር ከዚህ ቀደም አልሰማነውምን?” በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። አድማጮች እውነትን ይበልጥ በተሟላ መንገድ መረዳትና ማስተዋል እንዲችሉ መደጋገም እንዴት እንደረዳቸው እንዲናገሩ ጋብዝ።—መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 15, 1995 ገጽ 21-2 እና ነሐሴ 15, 1993 ገጽ 13-14 አንቀጽ 10-12ን ተመልከት።
መዝሙር 100 (222) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 13 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 74 (168)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ፦ “የ2000 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት።” በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት የበላይ ተመልካች የሚቀርብ ንግግር። ለአዲሱ ዓመት በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ የተደረገውን የሚከተለውን ለውጥ ተናገር። ክፍል ቁ. 3 የቤተሰብ ደስታ ከተባለው መጽሐፍ መቅረቡ ይቀጥልና ከዚያም በዓመቱ የመጨረሻ ሦስት ወራት ይህ ክፍል “መጽሐፍ ቅዱሳዊ የውይይት አርእስት” ከተባለው ቡክሌት ላይ ይቀርባል። ሁሉም ሳምንታዊውን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ በፕሮግራሙ መሠረት እንዲያነቡና በትምህርት ቤቱ የሚሰጣቸውን ክፍል ተዘጋጅተው ለማቅረብ ትጋት እንዲያሳዩ አበረታታ።
20 ደቂቃ፦ “በአምላክ መኖር የማያምን ሰው ቢያጋጥማችሁ ምን ትሉታላችሁ?” ጥያቄና መልስ። ብዙዎች በአምላክ ላይ እምነት እንዲያጡ ያደረጓቸውን የተለያዩ ምክንያቶች ተናገር። የአምላክን መኖር እንድንቀበል የሚያደርጉንን አሳማኝ ምክንያቶች እንዲገነዘቡ በመርዳት እነርሱን ማነጋገር የምንችልባቸውን አንዳንድ መንገዶች ጥቀስ። አንድ ወይም ሁለት አጠር ያሉ ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። ተጨማሪ ሐሳብ ለማግኘት ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 146-52ን እና የሰው ልጅ አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ (እንግሊዝኛ) ከተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 14ን ተመልከት።
መዝሙር 98 (220) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 20 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 65 (152)
7 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች በቅርቡ መስክ አገልግሎት ላይ ያጋጠሟቸውን ተስማሚ የሆኑ አጠር ያሉ ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ።
18 ደቂቃ፦ “የኤድስ ተጠቂዎችን መርዳት።” የሚያዝያ—ሰኔ 1995 ንቁ! ገጽ 18-19 እና የጥር 1999 ገጽ 4 እና 5 እንዲሁም በገጽ 9 በሚገኘው ሣጥን ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። እባክህ፣ የኤች አይ ቪ ተሸካሚና የኤድስ ተጠቂ ለሆኑ ሰዎች ደግነት ማሳየት አስፈላጊ መሆኑን እንዲሁም በተለይ ለማግባት የሚያስቡ ሰዎች ማስተዋል የተሞላበት ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አጉላ። በተጨማሪም በበሽታው የተለከፉ ሰዎች ጉዳዩን ለሽማግሌዎች ማሳወቅ እንዳለባቸው ተናገር። እንዲሁም እንክብካቤ የሚያደርጉላቸው ሰዎች ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዲችሉ ጉዳዩ ሊነገራቸው እንደሚገባ ግለጽ።
20 ደቂቃ፦ ከሃይማኖታዊ ድርጅት ጋር ግንኙነት ባለው ሥራ ላይ ተቀጥሬ መሥራት እችላለሁን? በሚያዝያ 15, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 28-30 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። አንዳንዶች በእንዲህ ዓይነት ሥራ ተቀጥረው መሥራት ከጀመሩ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የሚሠሩት ነገር ከመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ጋር የሚጋጭ መሆኑን ተገንዝበዋል። አንድ ዓይነት ሃይማኖታዊ ንክኪ ባላቸው ዓለማዊ ሥራዎች ተቀጥሮ መሥራትን በተመለከተ ውሳኔ ስናደርግ ልንመረምራቸው የሚገቡትን ጥያቄዎች ተናገር። ሁሉም በይሖዋ ፊት ጥሩ አቋም እንዲኖራቸው የሚያስችል ጎዳና እንዲከተሉ አበረታታ።—2 ቆሮ. 6:3, 4, 14-18
መዝሙር 66 (155) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 27 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 73 (166)
7 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በአዲሱ ዓመት የጉባኤያችሁ የስብሰባ ሰዓት የሚቀይር ከሆነ ሁሉም በአዲሱ ሰዓት አዘውትረው መሰብሰባቸውን እንዲቀጥሉ በማሳሰብ ደግነት የተሞላበት ማበረታቻ ስጥ። ለመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችና ፍላጎት ላላቸው ሰዎች የተደረገውን ለውጥ አሳውቁ። እንዲሁም አዲሱን ፕሮግራም በያዙ መጋበዣ ወረቀቶች መጠቀም ጀምሩ። ሁሉም የታኅሣሥ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱና ለሚቀጥለው ሳምንት የኅዳር የመንግሥት አገልግሎታችንን ይዘው እንዲመጡ አሳስብ።
18 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥኑን በጥያቄና መልስ አቅርብ። የምትወዱት ሰው ሲሞት ከተባለው ብሮሹር በገጽ 20-24 ላይ ካሉት ሐሳቦች አንዳንዶቹን በአጭሩ ጥቀስ።
20 ደቂቃ፦ በጥር ወር የቆዩ መጻሕፍትን ማበርከት። በንግግርና በሠርቶ ማሳያዎች የሚቀርብ። በጉባኤው የሚገኙ ከ1986 በፊት የታተሙ ሁለት ወይም ሦስት ባለ 192 ገጽ የቆዩ መጻሕፍት አሳይና አስፋፊዎች በመስክ አገልግሎት የሚጠቀሙበት የተወሰነ መጽሐፍ እንዲወስዱ አበረታታ። ልናበረክታቸው ከምንችለው ጽሑፎች መካከል ወጣትነትህ፣ የቤተሰብ ኑሮ፣ መንግሥትህ ትምጣ፣ በሕይወት መትረፍ፣ አምልኮ ይገኙበታል። ሰዎች ለመጽሐፍ ቅዱስ ፍላጎት እንዲያሳዩ በማድረግ ረገድ እነዚህ የቆዩ ጽሑፎች አሁንም ውጤታማ የሆኑበትን ምክንያት ግለጽ። በእያንዳንዱ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙትን ውይይት በመጀመር ረገድ ጥሩ አድርገን ልንጠቀምባቸው የምንችል የመነጋገሪያ ነጥቦችንና ሥዕሎችን ጎላ አድርገህ ግለጽ። አንድ ወይም ሁለት አቀራረቦችን በሠርቶ ማሳያ አቅርብ። ፍላጎት ያሳየ ሰው ሲገኝ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው በተባለው ብሮሹር በመጠቀም ጥናት ማስጀመር ይቻላል።
መዝሙር 44 (105) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 3 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 5 (10)
8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
17 ደቂቃ፦ ምን ብላችሁ እንደምትመልሱ እወቁ። (ቆላ. 4:6) በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለሌሎች ለማካፈል ሁኔታዎችን በማመቻቸት ረገድ ማመራመር የተባለው መጽሐፍ ግሩም እገዛ ያደርግልናል። አንድ የቤት ባለቤት ከምናምንባቸው ነገሮች በአንዱ ላይ የተቃውሞ ሐሳብ ቢሰነዝር ስለ ጉዳዩ በሚናገረው የምዕራፉ መጨረሻ ላይ በሚገኘው “አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ—” በሚለው ክፍል ያለውን ሐሳብ መጠቀም እንችላለን። ማመራመር መጽሐፍ በገጽ 29, 63-66, 73-75, 78-79,103-4,138 ላይ “አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ . . .” በሚለው ክፍል ሥር ከቀረቡት መካከል በአገልግሎት ክልላችሁ ውስጥ ጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉትን መርጠህ አቅርብ።
20 ደቂቃ፦ “ሙስሊም ቢያጋጥማችሁ ምን ትላላችሁ?” በኅዳር 1999 የመንግሥት አገልግሎታችን የመጨረሻ ገጽ ላይ የወጣው ርዕስ በጥያቄና መልስ ይቀርባል። የተለየ ባሕል ካላቸው ሰዎች ጋር ስንነጋገር ማስተዋል መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነ ጎላ አድርገህ ግለጽ። ጥሩ ዝግጅት የተደረገበት አቀራረብ በሠርቶ ማሳያ አቅርብ። ስለ እስልምና ሃይማኖት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 23-4ን እንዲሁም የሰው ዘር አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ (እንግሊዝኛ) ከተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 12ን ተመልከት።
መዝሙር 26 (56) እና የመደምደሚያ ጸሎት።