የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ታኅሣሥ 8 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 7 (19)
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የነሐሴን ወር ሪፖርትና “የ2008 የአገልግሎት ዓመት ጎላ ያሉ ገጽታዎች” የሚለውን ከልስ። ጉባኤያችሁ ለዚህ ሪፖርት መገኘት ያደረገውን አስተዋጽኦ ተናገር። የኅዳር 1 መጠበቂያ ግንብ እና የኅዳር ንቁ! መጽሔቶች ለማበርከት የሚያስችሉትን በገጽ 10 ላይ የሚገኙ የናሙና አቀራረቦች በአጭሩ ከልስ። እነዚህን መጽሔቶች በማበርከት የተሳካላቸው አስፋፊዎች መጽሔቶቹን እንዴት እንዳበረከቷቸው እንዲናገሩ ጋብዝ። ያስተዋወቁት የትኛውን ርዕስ ነው? ምን ጥያቄና የትኛውንስ ጥቅስ ተጠቀሙ?
15 ደቂቃ፦ የ2009 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት። በትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች የሚቀርብ ንግግር። ከኅዳር 2008 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ ለጉባኤው የሚያስፈልጉ አንዳንድ ነጥቦችን ጥቀስ። ረዳት ምክር ሰጪው ያለውን ኃላፊነት ተናገር። ሁሉም ክፍል ሲሰጣቸው ተገኝተው በማቅረብ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጎላ ያሉ ነጥቦች ላይ ሐሳብ በመስጠት እንዲሁም በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም ከተባለው መጽሐፍ ላይ በየሳምንቱ የሚሰጡትን ሐሳቦች ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ትጉዎች እንዲሆኑ አበረታታ።
15 ደቂቃ፦ “ማመራመር የተባለውን መጽሐፍ እየተጠቀማችሁበት ነው?”* አንቀጽ 4ን ስትወያዩ አንድ የዘወትር አቅኚ ወይም ብቃት ያለው አስፋፊ ከቤት ወደ ቤት በሚያገለግልበት ጊዜ ‘የይሖዋ ምሥክሮች የገናን በዓል የማያከብሩት ለምንድን ነው?’ ለሚለው ጥያቄ የማመራመር መጽሐፍን ተጠቅሞ እንዴት መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ።
መዝሙር 3 (6)
ታኅሣሥ 15 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 71 (163)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። “አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም” በሚለው ርዕስ ላይ ተወያዩ። ስብሰባው የሚደረግበት ቀን የሚታወቅ ከሆነ ተናገር።
10 ደቂቃ፦ የመደጋገምን ዘዴ በአገልግሎት ላይ ተጠቀሙበት። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 207 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በአንቀጾቹ ውስጥ በተጠቀሰው ሐሳብ ላይ የተመሠረቱ አንድ ወይም ሁለት አጫጭር ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
25 ደቂቃ፦ “በአፓርታማዎች ውስጥ ‘በሚገባ መመሥከር’”* በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ወይም በሌላ ሽማግሌ የሚቀርብ። ክፍሉን ለክልሉ እንደሚስማማ አድርገህ አቅርበው።
መዝሙር 68 (157)
ታኅሣሥ 22 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 23 (48)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን የምስጋና ደብዳቤ አንብብ። በጥር ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። ከዚያም አንድ የጉባኤ ሽማግሌ ጽሑፉን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ።
15 ደቂቃ፦ የታኅሣሥ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የታኅሣሥ ንቁ! መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። የመጽሔቶቹን ይዘት በአጭሩ ከተናገርክ በኋላ በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ሰዎችን ሊማርኩ ይችላሉ የሚሏቸውን ርዕሶች እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ። እንዲህ ያሉበትን ምክንያት እንዲናገሩ ጠይቃቸው። አንዳንድ ርዕሶችን እንደ ምሳሌ በማንሳት፣ አድማጮች ውይይት ለመጀመር ምን ጥያቄዎችን ለመጠቀም እንዳሰቡና መጽሔቶቹን ከማበርከታቸው በፊት ከርዕሱ ውስጥ የትኛውን ጥቅስ ሊያነቡ እንደሚችሉ ጠይቃቸው። ክፍሉን ከመደምደምህ በፊት በገጽ 10 ላይ የሚገኙትን የናሙና መግቢያዎች ወይም ለክልሉ ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
20 ደቂቃ፦ “ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያጠኑ የምንጋብዝበት ልዩ ቀን”* በጥር ወር ውስጥ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያጠኑ ለመጋበዝ የታሰበው በየትኛው ቅዳሜና እሁድ እንደሆነ ለጉባኤው ተናገር። በአንቀጽ 3 ላይ ያሉትን ሐሳቦች ከከለስክ በኋላ አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
መዝሙር 55 (133)
ታኅሣሥ 29 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 81 (181)
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bh ምዕ. 8 አን. 18-23፤ ተጨማሪ ክፍል ገጽ 215-218
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ራእይ 15-22
የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
የአገልግሎት ስብሰባ፦
መዝሙር 38 (85)
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ፦ “የስብከቱ ሥራ ጽናት ይጠይቃል።”* ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሱት ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ።
መዝሙር 66 (155)
ጥር 5 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 15 (35)
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bh ምዕ. 9 አን. 1-9፤ ተጨማሪ ክፍል ገጽ 218-219
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 1-5
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 3:1-15
ቁ. 2፦ ኢየሱስ ታላቅ አስተማሪ የነበረው ለምንድን ነው? (lr ምዕ. 1)
ቁ. 3፦ ከንቱ ያልሆነው ነገር ምንድን ነው? (1 ቆሮ. 15:58)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
መዝሙር 43 (98)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
25 ደቂቃ፦ መንፈሳዊ የልብ ድካም እንዳይዝህ መከላከል ትችላለህ። በታኅሣሥ 1, 2001 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 9-13 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።
መዝሙር 49 (114)
[የግርጌ ማስታወሻዎች ]
አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።