መጋቢት 12 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መጋቢት 12 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 40 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
fy ምዕ. 7 ከአን. 9-13 እና ሣጥን (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 5-7 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ኤርምያስ 5:15-25 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ በድሮ ጊዜ በወንድምና በእህት መካከል ይደረግ የነበረውን ጋብቻ አምላክ ለምን ፈቀደ?—rs ገጽ 252 አን. 3, 4 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ይሖዋ ሕዝቦቹን ከመንፈሳዊ አደጋዎች የሚጠብቀው እንዴት ነው? (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ የማስተማር ችሎታችሁን አዳብሩ።—ክፍል 2 በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 57 አንቀጽ 3 አንስቶ በገጽ 59 ላይ እስከሚገኘው ንዑስ ርዕስ ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በንግግር የሚቀርብ።
10 ደቂቃ፦ የምስጋና መሥዋዕት ዘወትር ለአምላክ አቅርቡ። (ዕብ. 13:15) በ2011 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) በገጽ 59 አንቀጽ 1, 2 እንዲሁም በገጽ 70 አንቀጽ 7 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። ምን ትምህርት እንዳገኙ አድማጮችን ጠይቅ።
10 ደቂቃ፦ “ይህን ሁልጊዜ . . . አድርጉት።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። ጉባኤያችሁ የመታሰቢያውን በዓል የሚያከብርበትን ሰዓትና ቦታ ተናገር።
መዝሙር 5 እና ጸሎት