የኋለኛውን ገጽ ተመልከቱ
የምኑን ኋለኛ ገጽ? ያለፉትን የመንግሥት አገልግሎታችን እትሞች ኋለኛ ገጽ ማለታችን ነው። በዚህ ወርና በሚቀጥለው ወር በአገልግሎታችን የምንጠቀምባቸውን የተለያዩ ብሮሹሮች እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሐሳቦች ለማግኘት የሐምሌና የነሐሴ 1995 እና 1996 እትሞች እንዲሁም የሐምሌ 1998ን እትም ተመልከቱ። በተጨማሪም ያለፈው ዓመት የሐምሌ እትም በገጽ 7 ላይ በጣም ማራኪ ሃሳብ ይዟል።