የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 9/12 ገጽ 1
  • አቀራረባችሁ ውጤታማ ይሁን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አቀራረባችሁ ውጤታማ ይሁን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘በቃሌ ኑሩ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • “የግለሰቡን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉ የቆዩ መጽሔቶችን ወይም ብሮሹሮችን አበርክቱ”
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • “ለሁሉም ዓይነት ሰዎች” ስበኩ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች ስታገኝ ተመልሰህ ጠይቃቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
km 9/12 ገጽ 1

አቀራረባችሁ ውጤታማ ይሁን

1. የጥንቶቹ ክርስቲያኖች አቀራረባቸውን ይቀያይሩ እንደነበር ማወቃችን ምን ያስተምረናል?

1 የጥንቶቹ ክርስቲያኖች ምሥራቹን የተለያየ ባሕልና ሃይማኖት ላላቸው ሰዎች ሰብከዋል። (ቆላ. 1:23) መልእክቱ የሚናገረው ስለ አንድ ነገር ይኸውም ስለ አምላክ መንግሥት ቢሆንም የአድማጮችን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት አቀራረባቸውን ይቀያይሩ ነበር። ለምሳሌ ያህል፣ ጴጥሮስ ለቅዱሳን መጻሕፍት ከፍተኛ አክብሮት ለነበራቸው አይሁዳውያን ሲሰብክ ንግግሩን የጀመረው የኢዩኤልን ትንቢት በመጥቀስ ነው። (ሥራ 2:14-17) በሌላ በኩል ደግሞ ጳውሎስ ከግሪካውያን ጋር ሲወያይ ምን እንዳደረገ ከ⁠የሐዋርያት ሥራ 17:22-31 ላይ መመልከት ይቻላል። በዛሬው ጊዜም ቢሆን ለቅዱሳን መጻሕፍት አክብሮት ያላቸው ሰዎች ባሉበት አካባቢ ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል በነፃነት መጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅመን ማወያየት እንችላለን። ለመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ለሃይማኖት ግድየለሽ የሆኑ ሰዎችን ስናነጋግር አሊያም የክርስትናን እምነት ለማይከተሉ ሰዎች ስንመሠክር ግን ይበልጥ ብልሃተኞች መሆን ሊጠበቅብን ይችላል።

2. ለመጽሐፍ ቅዱስ አክብሮት ያላቸውንም ሆነ የሌላቸውን ሰዎች በምናነጋግርበት ጊዜ በወሩ ውስጥ የምናበረክታቸውን ጽሑፎች መጠቀም ያለብን እንዴት ነው?

2 በወሩ ውስጥ የሚበረከቱ ጽሑፎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ተጠቀሙ፦ በያዝነው የአገልግሎት ዓመት የምናበረክታቸው ጽሑፎች በየሁለት ወሩ የሚቀያየሩ ሲሆን ትኩረት የምናደርገው መጽሔቶችን፣ ትራክቶችንና ብሮሹሮችን በማበርከት ላይ ነው። በአካባቢያችን ያሉ ሰዎች ለመጽሐፍ ቅዱስ ግድ የለሽ ቢሆኑም እንኳ የእነሱን ትኩረት የሚስቡ ጽሑፎችን ለማሳየት ጥረት እናደርጋለን። የቤቱን ባለቤት መጀመሪያ ላይ ባገኘንበት ወቅት ጥቅስ ባናነብለትም ወይም ስለ መጽሐፍ ቅዱስ በቀጥታ ባናነሳለትም እንኳ ፍላጎት ካሳየ በፈጣሪና በመንፈስ መሪነት ባጻፈው ቃሉ ላይ እምነት እንዲያሳድር የመርዳት ግብ ይዘን ተመላልሶ መጠየቅ ልናደርግለት እንችላለን። በሌላ በኩል ደግሞ ለመጽሐፍ ቅዱስ አክብሮት ያላቸው ሰዎች በሚኖሩበት አካባቢ የምንሰብክ ከሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ትኩረት የሚያደርጉ ጽሑፎችንና አቀራረቦችን መጠቀም እንችላለን። እንዲያውም በወሩ ውስጥ የሚበረከተው ጽሑፍ ምንም ይሁን ምን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ አሊያም አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ የተባሉትን ብሮሹሮች ልናበረክት እንችላለን። ዋናው ነገር የሰዎችን ትኩረት የሚስብ አቀራረብ መጠቀማችን ነው።

3. የሰዎች ልብ ከአፈር ጋር የተመሳሰለው እንዴት ነው?

3 አፈሩን ማዘጋጀት፦ የሰዎች ልብ በአፈር ተመስሏል። (ሉቃስ 8:15) የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በአንዳንድ ሰዎች ውስጥ ሥር እንዲሰድና እንዲያድግ ከተፈለገ አፈሩን ለማዘጋጀት የበለጠ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል። በመጀመሪያው መቶ ዘመን የኖሩ ወንጌላውያን በተለያዩ የአፈር ዓይነቶች ላይ የእውነትን ዘር መትከል የቻሉ ሲሆን ይህም እርካታና ደስታ አስገኝቶላቸዋል። (ሥራ 13:48, 52) እኛም በተመሳሳይ ለአቀራረባችን ትኩረት የምንሰጥ ከሆነ ውጤታማ እንሆናለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ