የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ማስጀመር
“ብዙ ሰዎች የኢየሱስን ልደት ያከብራሉ፤ ይሁንና የኢየሱስንስ ሞት ማክበር አስፈላጊ ይመስልዎታል?” ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም የመጋቢት 1ን መጠበቂያ ግንብ ስጠውና ገጽ 16 ላይ በሚገኘው በመጀመሪያው ንዑስ ርዕስ ሥር ያለውን ሐሳብ አብራችሁ ተመልከቱ፤ በተጨማሪም እዚያ ላይ ከተጠቀሱት ጥቅሶች መካከል ቢያንስ አንዱን አብራችሁ አንብቡ። ከዚያም በቀጣዩ ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
መጋቢት 1 መጠበቂያ ግንብ
“የተለያዩ እምነቶችና ልማዶች ያሏቸው በርካታ ቤተ ክርስቲያኖችና ሃይማኖታዊ ቡድኖች አሉ። ሆኖም “ክርስቲያን” ነን የሚሉ ሁሉ በእርግጥ ክርስቲያኖች ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ኢየሱስ በዮሐንስ 13:34, 35 ላይ እውነተኛ ክርስቲያኖችን ለይቶ የሚያሳውቅ አንድ ምልክት ተናግሯል። [ጥቅሱን አንብብ።] ይህ መጽሔት እውነተኛ ክርስቲያኖችን ለይተን ለማወቅ የሚያስችሉንን ኢየሱስ የተናገራቸውን አምስት ነጥቦች ያብራራል።”
መጋቢት ንቁ!
“በሰዎች ዘንድ እየተለመደ ስለመጣ አንድ አሳሳቢ ችግር ከጎረቤቶችዎ ጋር እየተወያየን ነበር። በዛሬው ጊዜ ሰዎች ቁጣቸውን መቆጣጠር እያቃታቸውና ከበፊቱ የበለጠ ግልፍተኞች እየሆኑ የመጡ ይመስላል። ይህ የሆነበት ምክንያት ምን ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ በመዝሙር 37:8 ላይ ስለ ቁጣ ምን እንደሚል ልብ ይበሉ። [ጥቅሱን አንብብ።] ይህ መጽሔት በዛሬው ጊዜ ሰዎች ቁጡ የሆኑበትን ምክንያትና ቁጣችንን መቆጣጠር የምንችልባቸውን መንገዶች ይጠቁማል።”