ዘሌዋውያን 19:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ባልንጀራህን አታጭበርብር፤+ አትዝረፈውም።+ የቅጥር ሠራተኛውን ደሞዝ ሳትከፍል አታሳድር።+ ማቴዎስ 10:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ወርቅ ወይም ብር አሊያም መዳብ በመቀነታችሁ አትያዙ፤+ 10 ወይም ለጉዞ የምግብ ከረጢት ወይም ሁለት ልብስ* ወይም ትርፍ ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤+ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና።+ ሉቃስ 10:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ለሠራተኛ ደሞዙ ስለሚገባው+ ያቀረቡላችሁን ነገር እየበላችሁና እየጠጣችሁ+ በዚያው ቤት ቆዩ።+ ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው ቤት አትዘዋወሩ። ገላትያ 6:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ከዚህም በተጨማሪ ቃሉን በመማር ላይ ያለ ማንኛውም ሰው፣ ይህን ትምህርት* ከሚያስተምረው ሰው ጋር መልካም ነገሮችን ሁሉ ይካፈል።+
9 ወርቅ ወይም ብር አሊያም መዳብ በመቀነታችሁ አትያዙ፤+ 10 ወይም ለጉዞ የምግብ ከረጢት ወይም ሁለት ልብስ* ወይም ትርፍ ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤+ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና።+