መዝሙር
አራተኛ መጽሐፍ
(መዝሙር 90-106)
የእውነተኛው አምላክ ሰው የሙሴ ጸሎት።+
90 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ መኖሪያችን* ሆነሃል።+
3 ሟች የሆነ ሰው ወደ አፈር እንዲመለስ ታደርጋለህ፤
“የሰው ልጆች ሆይ፣ ወደ አፈር ተመለሱ”+ ትላለህ።
6 ጠዋት ላይ ሣሩ ያቆጠቁጣል፤ ደግሞም ይለመልማል፤
ምሽት ላይ ግን ጠውልጎ ይደርቃል።+
7 በቁጣህ አልቀናልና፤+
ከታላቅ ቁጣህም የተነሳ ተሸብረናል።
ይህም በችግርና በሐዘን የተሞላ ነው፤
ፈጥኖ ይነጉዳል፤ እኛም እናልፋለን።+
11 የቁጣህን ኃይል መረዳት የሚችል ማን ነው?
ቁጣህ፣ አንተ መፈራት የሚገባህን ያህል ታላቅ ነው።+
12 ጥበበኛ ልብ ማግኘት እንችል ዘንድ፣
ዕድሜያችንን እንዴት መቁጠር እንዳለብን አስተምረን።+
13 ይሖዋ ሆይ፣ ተመለስ!+ ይህ ሁኔታ የሚቀጥለው እስከ መቼ ነው?+
ለአገልጋዮችህ ራራላቸው።+
16 አገልጋዮችህ ሥራህን ይዩ፤
ልጆቻቸውም ግርማህን ይመልከቱ።+
17 የአምላካችን የይሖዋ ሞገስ በእኛ ላይ ይሁን፤
የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ አድርግልን።*
አዎ፣ የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ አድርግልን።+