መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት።
5 ትዕቢተኞች በስውር ወጥመድ አስቀመጡብኝ፤
ከመንገዱ አጠገብ የመረባቸውን ገመድ ዘረጉብኝ።+
አሽክላም አስቀመጡብኝ።+ (ሴላ)
6 ይሖዋን እንዲህ እለዋለሁ፦ “አንተ አምላኬ ነህ።
ይሖዋ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስማ።”+
7 ኃያል አዳኜ የሆንከው ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣
በጦርነት ቀን ራሴን ትከልላለህ።+
8 ይሖዋ ሆይ፣ የክፉዎች ምኞት እንዲሳካ አታድርግ።
ራሳቸውን ከፍ ከፍ እንዳያደርጉ፣ ሴራቸው እንዲሰምር አትፍቀድ።+ (ሴላ)
9 ዙሪያዬን የከበቡኝን ሰዎች ራስ፣
የገዛ ከንፈራቸው የተናገረው ክፋት ይሸፍነው።+
10 የእሳት ፍም በላያቸው ይውረድ።+
11 ስም አጥፊ በምድር* ላይ አንዳች ቦታ አያግኝ።+
ጨካኞችን ክፋት አሳዶ ይምታቸው።
12 ይሖዋ ለችግረኛው እንደሚሟገትና
ለድሃው ፍትሕ እንደሚያሰፍን አውቃለሁ።+
13 በእርግጥ ጻድቃን ለስምህ ምስጋና ያቀርባሉ፤
ቅኖችም በፊትህ ይኖራሉ።+