ኢሳይያስ
2 በእርግጥ ያብባል፤+
ሐሴት ያደርጋል፤ በደስታም እልል ይላል።
የይሖዋን ክብር፣ የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ።
3 የደከሙትን እጆች አበርቱ፤
የሚብረከረኩትንም ጉልበቶች አጽኑ።+
4 በጭንቀት የተዋጠ ልብ ላላቸው እንዲህ በሏቸው፦
“በርቱ፤ አትፍሩ።
እነሆ፣ አምላካችሁ ሊበቀል ይመጣል፤
አምላክ ብድራት ሊከፍል ይመጣል።+
እሱ መጥቶ ያድናችኋል።”+
በምድረ በዳ ውኃ ይፈልቃልና፤
በበረሃማ ሜዳም ጅረት ይፈስሳል።
7 በሐሩር የተቃጠለው ምድር ቄጠማ የሞላበት ኩሬ፣
የተጠማውም ምድር የውኃ ምንጭ ይሆናል።+
ቀበሮዎች ይኖሩበት የነበረው ጎሬ+
ለምለም ሣር፣ ሸምበቆና ደንገል ይበቅልበታል።
8 በዚያም አውራ ጎዳና ይኖራል፤+
ደግሞም “የቅድስና ጎዳና” ተብሎ ይጠራል።
ንጹሕ ያልሆነ ሰው አይጓዝበትም።+
ጎዳናው፣ በመንገዱ ላይ ለሚሄዱት ብቻ ይሆናል፤
ሞኞችም አይሄዱበትም።
9 በዚያ አንበሳ አይኖርም፤
አዳኝ አራዊትም ወደዚያ አይወጡም።
10 ይሖዋ የዋጃቸው ይመለሳሉ፤+ ወደ ጽዮንም በእልልታ ይመጣሉ።+
ፍጻሜ የሌለው ደስታን እንደ አክሊል ይጎናጸፋሉ።+
ደስታንና ሐሴትን ያገኛሉ፤
ሐዘንና ሲቃም ከዚያ ይርቃሉ።+