ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት የጽሑፍ ክለሳ
በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከመስከረም 6 እስከ ታኅሣሥ 20, 1999 በነበሩት ሳምንታት በተሰጡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ መጽሐፍ ተዘግቶ የሚደረግ የጽሑፍ ክለሳ። በሌላ ወረቀት ተጠቅመህ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ የቻልከውን ያህል ለብዙ ጥያቄዎች መልስ ስጥ።
[ማሳሰቢያ:- በጽሑፍ ክለሳው ወቅት ለማንኛውም ጥያቄ መልስ ለመፈለግ ማየት የሚፈቀደው መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ነው። በቅንፍ ውስጥ የተጠቀሱት ጽሑፎች በግልህ ምርምር እንድታደርግባቸው የቀረቡ ናቸው። የትኛው መጠበቂያ ግንብ እንደሆነ በሚጠቀስበት ጊዜ አንቀጹ የተሰጠው በሁሉም ቦታ ላይ አይደለም።]
ቀጥሎ ያለውን እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገር እውነት ወይም ሐሰት እያልክ መልስ:-
1. ይሖዋ የሰው ልጆች ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ የፈቀደው እርሱ የሚያስተዳድርበት መንገድ ምንጊዜም ትክክለኛና ፍትሐዊ መሆኑን ለማረጋገጥ ሲል ነው። (ዘዳ. 32:4፤ ኢዮብ 34:10-12፤ ኤር. 10:23) [w97 2/15 ገጽ 5 አን. 3]
2. መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ማንኛውንም ዓይነት ማማረር እንደሚያወግዝ ያሳያል። [w97 12/1 ገጽ 30 አን. 3-4]
3. ወላጆች ልጆቻቸውን ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ለመያዝ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች ማላላት አያስፈልጋቸውም። [fy ገጽ 108 አን. 14]
4. ማርቆስ 6:31-34 እንደሚያሳየው ኢየሱስ ለሕዝቡ ያዘነው የጤና እክልና ድህነት ስለነበረባቸው ብቻ ነው። [w97 12/15 ገጽ 29 አን. 1]
5. የሌሎች በጎች ክፍል የሆነ አንድ ክርስቲያን በኢየሱስ ሞት መታሰቢያ በዓል ላይ መገኘት ሳይችል ቢቀር በዘኁልቁ 9:10, 11 ላይ ከተገለጸው መሠረታዊ ሥርዓት ጋር በሚስማማ መንገድ በዓሉን ከአንድ ወር በኋላ ማክበር አለበት። (ዮሐ. 10:16) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w93 2/1 ገጽ 31 አን. 9ን ተመልከት።]
6. ምሳሌ 6:30 ስርቆት እንደ ስህተት የማይታይባቸው አንዳንድ ሁኔታዎች መኖራቸውን ያሳያል። [g98 መጋቢት ገጽ 23 አን. 2]
7. ዊልያም ቲንደል በ1530 ባዘጋጀው የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች የእንግሊዝኛ ትርጉም ላይ ጅሆቫ የሚለውን የአምላክ ስም በመጠቀም የመጀመሪያው ሰው ሆኗል። [w97 9/15 ገጽ 28 አን. 2]
8. በአሁኑ ጊዜ፣ የመማፀኛ ከተማ አምላክ ስለ ደም ቅድስና ያወጣውን ትእዛዝ በመጣሳችን ምክንያት ከሚመጣብን ሞት የሚጠብቀን የአምላክ ዝግጅት ነው። (ዘኁ. 35:11) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w95 11/15 ገጽ 17 አን. 8ን ተመልከት።]
9. የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ የሆነው ዘዳግም ሕጉ እንዲሁ በድጋሚ የሠፈረበት መጽሐፍ ብቻ ስለሆነ የስሙ ትርጉም “ሁለተኛ ሕግ” የሚል መሆኑ ተገቢ ነው። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ si ገጽ 36 አን. 4ን ተመልከት።]
ቀጥሎ ያሉትን ጥያቄዎች መልስ:-
10. ሊቀ ካህናቱ በጰንጠቆስጤ በዓል ወቅት ያቀርባቸው የነበሩት ሁለቱ በእርሾ የተጋገሩ ኅብስቶች የሚያመለክቱት ነገር ምንድን ነው? (ዘሌ. 23:15-17) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w98 3/1 ገጽ 13 አን. 21ን ተመልከት።]
11. የክርስትና ኢዮቤልዩ የጀመረው መቼ ነው? በዚያን ጊዜስ ምን ዓይነት ነፃነት አስገኝቷል? (ዘሌ. 25:10) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w95 5/15 ገጽ 24 አን. 14ን ተመልከት።]
12. በዘኁልቁ መጽሐፍ ላይ በሰፈረው ዘገባ መሠረት ከጥፋት መዳናችን በየትኞቹ ሦስት ነገሮች ላይ ይመካል? [si ገጽ 30 አን. 1]
13. ሙሴ የቅናት መንፈስ እንደሌለው በማሳየት ረገድ ጥሩ ምሳሌ የሆነው እንዴት ነው? (ዘኁ. 11:29) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w95 9/15 ገጽ 18 አን. 11ን ተመልከት።]
14. ማየት ሁልጊዜ ለማመን እንደማያበቃ የቆሬ፣ የዳታንና የአቤሮን ሁኔታ የሚያሳየው እንዴት ነው? [w97 3/15 ገጽ 4 አን. 2]
15. አንድ የቤተሰብ አባል ከባድ የጤና እክል ካጋጠመው ቤተሰቡ መቅደም ያለባቸውን ነገሮች ለመወሰን በቅድሚያ ሊወስዳቸው የሚገቡ እርምጃዎች ምንድን ናቸው? (ምሳሌ 15:22) [fy ገጽ 122 አን. 14]
16. በዘኁልቁ 26:64, 65 ላይ ጎላ ተደርጎ የተገለጸው አስፈላጊ ትምህርት ምንድን ነው? [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ gE 95 8/8 ገጽ 10-11 አን. 5-8ን ተመልከት።]
17. የፊንሐስ ምሳሌ ራስን ለይሖዋ መወሰን ምን ትርጉም እንዳለው እንድንገነዘብ የሚረዳን እንዴት ነው? (ዘኁ. 25:11) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w95 3/1 ገጽ 16-17 አን. 12-13ን ተመልከት።]
18. አንድ ሰው ከታላቁ የመማጸኛ ከተማ ‘ክልል ሊወጣ’ የሚችለው እንዴት ነው? (ዘኁ. 35:26) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w95 11/15 ገጽ 20 አን. 20ን ተመልከት።]
19. ኮዴክስ ሳይናይቲከስ ለመጽሐፍ ቅዱስ የትርጉም ሥራ በረከት የሆነው በምን መንገድ ነው? [w97 10/15 ገጽ 11 አን. 2]
ቀጥሎ ያለውን እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገር የሚያሟላውን ቃል (ቃላት) ወይም ሐረግ ስጥ:-
20. ይሖዋ ክፋት እንዲኖር የፈቀደው እሱ ብቻ____________________ መሆኑንና የሁሉም ፍጥረታቱ ሰላምና ደስታ ቀጣይነት እንዲኖረው ሕጎቹን_________________________ የግድ አስፈላጊ መሆኑን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማረጋገጥ ነው። (መዝ. 1:1-3፤ ምሳሌ 3:5, 6፤ መክ. 8:9) [w97 2/15 ገጽ 5 አን. 4]
21. የዘሌዋውያን መጽሐፍ ደም ጥቅም ላይ እንዲውል የተፈቀደበት ብቸኛው መንገድ_________________________ እንደሆነ በመግለጽ የደምን_________________________ በማጉላት ረገድ የላቀ ቦታ አለው። [si ገጽ 29 አን. 33]
22. ከመዝሙር 144:15 ጋር በሚስማማ መንገድ እውነተኛ ደስታ በእውነተኛ_________________________ እና ከይሖዋ አምላክ ጋር ባለን ጥሩ_________________________ ላይ የተመሠረተ የልብ ሁኔታ ነው። [w97 3/15 ገጽ 23 አን. 7]
23. ከዕብራይስጥ ወደ ተራ ግሪክኛ ተተርጉሞ በ150 ከዘአበ ገደማ የተጠናቀቀው መጽሐፍ ቅዱስ_________________ በመባል ይታወቃል። ጄሮም ወደ ላቲን የተረጎመው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ደግሞ_________________________ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ሥራው የተጠናቀቀው በ400 እዘአ ገደማ ነው። [w97 8/15 ገጽ 9 አን. 1፤ ገጽ 10 አን. 4]
24. ይሁዳ በዘኁልቁ መጽሐፍ ላይ ተመዝግቦ የሚገኘውን የበለዓምንና የቆሬን ታሪክ በመጥቀስ ክርስቲያኖች_________________________ እና_________________________ ወጥመድ ራሳቸውን እንዲጠብቁ አስጠንቅቋቸዋል። [si ገጽ 35 አን. 35]
25. ምንም እንኳ የብቸኝነት ስሜት ተአምራዊ ፈውስ ባይኖረውም አንድ ነጠላ ወላጅ ያለማቋረጥ_________________________ በማቅረብ_________________________ በሚገኝ ኃይል አማካኝነት ሊቋቋመው ይችላል። (1 ጢሞ. 5:5) [fy ገጽ 113 አን. 21]
ቀጥሎ ባለው በእያንዳንዱ ዓረፍተ ነገር ውስጥ ትክክለኛውን መልስ ምረጥ:-
26. በዓመት አንድ ጊዜ (በዳስ በዓል፣ በስርየት ቀን፣ በማለፍ በዓል) ላይ ይሖዋን የሚያመልኩ መጻተኞችን ጨምሮ መላው የእስራኤል ብሔር (ከማንኛውም ዓይነት ሥራ ነፃ መሆን፣ አስራት ማውጣት፣ የእህል በኩራት ማቅረብ) እና መጾም ነበረበት። (ዘሌ. 16:29-31) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w96 7/1 ገጽ 10 አን. 12ን ተመልከት።]
27. የአዲሲቱ ዓለም የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ኮሚቴ ከነበሩት ዓላማዎች አንዱ አንባብያን የመጀመሪያዎቹ ቋንቋዎች የነበራቸውን ለዛ እንዲያጣጥሙና ከዚያ ጋር የተያያዘውንም ሐሳብ ይበልጥ ማግኘት እንዲችሉ (በተቻለ መጠን ቃል በቃል የተቀመጠ፣ የመጀመሪያዎቹን ቋንቋዎች በቀላል አነጋገር በማስቀመጥ የቀረበ፣ ከአንድ የተወሰነ የመሠረተ ትምህርት ግንዛቤ ጋር የሚጣጣም) ትርጉም ማዘጋጀት ነው። [w97 10/15 ገጽ 11 አን. 5]
28. በዕብራውያን 13:19 መሠረት መሰል አማኞች ያለማቋረጥ የሚያቀርቡት ጸሎት (አምላክ በሚፈቅደው ነገር፣ አምላክ ነገሮችን በሚይዝበት መንገድ) ላይ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል። [w97 4/15 ገጽ 6 አን. 1]
29. እስራኤላውያን ‘በልብሳቸው ዘርፍ ላይ ሰማያዊ ፈትል እንዲያደርጉ’ የታዘዙት (ቅዱስ ጌጥ፣ የልከኝነት ምልክት፣ የይሖዋ ሕዝቦች እንደመሆናቸው መጠን ከዓለም የተለዩ እንደሆኑ የሚታይ ማስታወሻ) ሆኖ እንዲያገለግላቸው ነበር። (ዘኁ. 15:38, 39) [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w10-104 ገጽ 12 አን. 16]
30. የዘዳግም መጽሐፍ የሚሸፍነው የጊዜ ርዝመት (ሁለት ወር፣ አንድ ዓመት፣ ሁለት ዓመት) ሲሆን ተጽፎ የተጠናቀቀው ደግሞ በ (1513፣ 1473፣ 1467) ከዘአበ መጀመሪያ ላይ ነበር። [si ገጽ 36 አን. 6]
31. አንድ ቤተሰብ በመካከሉ የተከሰተውን ከባድ ሕመም በተሳካ ሁኔታ መቋቋም መቻል አለመቻሉ በአብዛኛው የተመካው የቤተሰቡ አባላት ባላቸው (የገንዘብ አቅም፣ አመለካከት፣ የመድህን ዋስትና) ላይ ነው። (ምሳሌ 17:22) [fy ገጽ 120 አን. 10]
ቀጥሎ ያሉትን ጥቅሶች ከታች ካሉት ሐሳቦች ጋር አዛምድ:-
ምሳሌ 1:8፤ ምሳሌ 5:3, 4፤ ዘኁ. 16:41, 49፤ ቆላ. 2:8
32. ምንም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ ልጆችን የማስተማሩን ኃላፊነት በዋነኛነት የሚሰጠው ለአባት ቢሆንም እናትም በዚህ ረገድ ከፍተኛ ሚና ትጫወታለች። [fy ገጽ 133 አን. 12]
33. ይሖዋ በተሾሙ አገልጋዮቹ አማካኝነት ፍትሕ እንዲጠበቅ በሚያደርግበት መንገድ ላይ ስህተት መፈላለግ አደገኛ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል። [ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፤ w96 6/15 ገጽ 21 አን. 13ን ተመልከት።]
34. ከፆታ ብልግና ፈተና ለመራቅ ድርጊቱ ተገቢ እንዳልሆነና አደገኛና መራራ መዘዝ እንደሚያስከትል ማስታወስ ይኖርብናል። [fy ገጽ 93 አን. 9]