የአቀራረብ ናሙናዎች
መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 1
“በዚህ አካባቢ ለምናገኛቸው ሰዎች ግሩም ርዕስ የያዘውን ይህን የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት እያሳየናቸው ነው። [የመጽሔቱን ሽፋን አሳየው።] አንዳንድ ሰዎች ጸሎትን የሚሰማ አካል ስለሌለ መጸለይ እንዲሁ ጊዜ ማባከን እንደሆነ ይሰማቸዋል። ሌሎች ግን አምላክ ጸሎታቸውን እንደሚሰማ ያምናሉ። እርስዎ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ ጸሎትን በተመለከተ ምን እንደሚል ባሳይዎት ደስ ይለኛል። [ኢሳይያስ 30:19ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አምላክ በትክክለኛ መንገድ የቀረበን ጸሎት እንደሚሰማና መልስ እንደሚሰጥ የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ይዟል።”
ንቁ! ጥቅምት
“አምላክ መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው? በሚለው ጥያቄ ዙሪያ ከሰዎች ጋር አጠር ያለ ውይይት እያደረግን ነው። እንዲህ ያለ ጥያቄ ማንሳት አምላክን እንደ መዳፈር ሊቆጠር ይችላል ብለው ያስባሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ጻድቅ ሰው የነበረው ኢዮብ በአንድ ወቅት ለአምላክ ጥያቄ ማቅረብ እንደሚፈልግ ገልጾ ነበር። [ኢዮብ 23:3-5ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ብዙ ሰዎች አምላክን የመጠየቅ አጋጣሚ ቢያገኙ ሊያነሷቸው የሚፈልጓቸውን ሦስት ጥያቄዎችና መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን አጥጋቢ መልስ ይዟል።”