የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 15:1-5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ይሖዋ ሆይ፣ በድንኳንህ ውስጥ በእንግድነት የሚስተናገድ ማን ነው?

      በተቀደሰ ተራራህ የሚኖር ማን ነው?+

       2 ያለነቀፋ* የሚመላለስ፣+

      ትክክል የሆነውን የሚያደርግ፣+

      በልቡም እውነትን የሚናገር ሰው ነው።+

       3 በአንደበቱ ስም አያጠፋም፤+

      በባልንጀራው ላይ መጥፎ ነገር አይሠራም፤+

      የወዳጆቹንም ስም አያጎድፍም።*+

       4 ነውረኛ የሆነን ሰው ሁሉ ይንቃል፤+

      ይሖዋን የሚፈሩትን ግን ያከብራል።

      ጉዳት ላይ ሊጥለው ቢችልም እንኳ ቃሉን* አያጥፍም።+

       5 ገንዘቡን በወለድ አያበድርም፤+

      ንጹሕ የሆነውን ሰው ለመወንጀልም ጉቦ አይቀበልም።+

      እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ሁሉ ፈጽሞ አይናወጥም።*+

  • መዝሙር 27:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  4 ይሖዋን አንድ ነገር ለመንኩት፤

      ምኞቴም ይኸው ነው፦

      በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በይሖዋ ቤት እኖር ዘንድ፣+

      ይሖዋ ደስ የሚያሰኝ መሆኑን በትኩረት እመለከት ዘንድ፣

      ቤተ መቅደሱንም በአድናቆት አይ* ዘንድ ነው።+

  • መዝሙር 84:1-4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 84 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣

      ታላቁ የማደሪያ ድንኳንህ ምንኛ ያማረ* ነው!+

       2 ሁለንተናዬ* የይሖዋን ቅጥር ግቢዎች

      እጅግ ናፈቀ፤

      አዎ፣ በጣም ከመጓጓቴ የተነሳ ዛልኩ።+

      ልቤም ሆነ ሥጋዬ ሕያው ለሆነው አምላክ እልል ይላል።

       3 ንጉሤና አምላኬ የሆንከው የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣

      ታላቁ መሠዊያህ ባለበት አቅራቢያ፣

      ወፍ እንኳ በዚያ ቤት ታገኛለች፤

      ወንጭፊትም ጫጩቶቿን የምታሳድግበት ጎጆ

      ለራሷ ትሠራለች።

       4 በቤትህ የሚኖሩ ደስተኞች ናቸው!+

      እነሱ ሁልጊዜ ያወድሱሃል።+ (ሴላ)

  • መዝሙር 84:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 በሌላ ቦታ አንድ ሺህ ቀን ከመኖር በቅጥር ግቢዎችህ አንዲት ቀን መዋል ይሻላልና!+

      በክፉዎች ድንኳን ከመኖር፣

      በአምላኬ ቤት ደጃፍ ላይ መቆም እመርጣለሁ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ