-
ዘዳግም 30:1-3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
30 “ይህ ቃል ሁሉ ይኸውም በፊትህ ያስቀመጥኩት በረከትና እርግማን+ በአንተ ላይ በሚመጣበትና አምላክህ ይሖዋ በመካከላቸው እንድትበተን ባደረገህ ብሔራት ምድር+ ሆነህ ይህን ቃል ሁሉ በምታስታውስበት* ጊዜ+ 2 እንዲሁም አንተም ሆንክ ልጆችህ እኔ ዛሬ በማዝህ ትእዛዝ ሁሉ መሠረት በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ*+ ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋ በምትመለሱበትና ቃሉን በምትሰሙበት ጊዜ+ 3 አምላክህ ይሖዋ ተማርከው የተወሰዱብህን ይመልስልሃል፤+ ምሕረትም ያሳይሃል፤+ እንዲሁም አምላክህ ይሖዋ በመካከላቸው እንድትበተን ካደረገህ ሕዝቦች ምድር ሁሉ መልሶ ይሰበስብሃል።+
-
-
ኢሳይያስ 43:6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ሰሜንን ‘ልቀቃቸው!’ እለዋለሁ፤+
ደቡብንም እንዲህ እለዋለሁ፦ ‘አታግታቸው።
ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ፣ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ አምጣ፤+
-
ኢሳይያስ 60:4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 ዓይንሽን አንስተሽ ዙሪያሽን ተመልከቺ!
ሁሉም አንድ ላይ ተሰብስበዋል፤ ወደ አንቺም እየመጡ ነው።
-
-
-