መዝሙር
137 በባቢሎን ወንዞች አጠገብ፣+ በዚያ ተቀምጠን ነበር።
ጽዮንን ባስታወስናት ጊዜ አለቀስን።+
3 የማረኩን ሰዎች በዚያ እንድንዘምርላቸው ጠየቁን፤+
የሚያፌዙብን ሰዎች በመዝሙር እንድናዝናናቸው
“ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን” አሉን።
4 የይሖዋን መዝሙር
በባዕድ ምድር እንዴት ልንዘምር እንችላለን?
7 ይሖዋ ሆይ፣ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀን
ኤዶማውያን ያሉትን አስታውስ፤
“አፍርሷት! ከሥረ መሠረቷ አፍርሷት!”+ ብለው ነበር።
9 ልጆችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጥ+
ደስተኛ ይሆናል።