ምሳሌ
ሂድና ባልንጀራህን በትሕትና አጥብቀህ ለምነው።+
4 ይህን ሳታደርግ አትተኛ፤
በዓይንህም እንቅልፍ አይዙር።
5 እንደ ሜዳ ፍየል ከአዳኝ እጅ፣
እንደ ወፍም ከወፍ አዳኝ እጅ ራስህን አድን።
6 አንተ ሰነፍ፣ ወደ ጉንዳን ሂድ፤+
መንገዷንም በጥሞና ተመልክተህ ጥበበኛ ሁን።
9 አንተ ሰነፍ፣ የምትጋደመው እስከ መቼ ነው?
ከእንቅልፍህ የምትነሳውስ መቼ ነው?
10 ቆይ ትንሽ ልተኛ፣ ቆይ ትንሽ ላንቀላፋ፣
እጄንም አጣጥፌ እስቲ ትንሽ ጋደም ልበል ካልክ፣+
11 ድህነት እንደ ወንበዴ፣
እጦትም መሣሪያ እንደታጠቀ ሰው ይመጣብሃል።+
15 በመሆኑም ጥፋት በድንገት ይመጣበታል፤
እንደማይጠገን ሆኖ በቅጽበት ይሰበራል።+
16 ይሖዋ የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፤
እንዲያውም እሱ የሚጸየፋቸው* ነገሮች ሰባት ናቸው፦
17 ትዕቢተኛ ዓይን፣+ ውሸታም ምላስ፣+ ንጹሕ ደም የሚያፈሱ እጆች፣+
18 ክፉ ሐሳብ የሚያውጠነጥን ልብና+ ወደ ክፋት በፍጥነት የሚሮጡ እግሮች፣
19 ባወራ ቁጥር ውሸት የሚናገር ሐሰተኛ ምሥክርና+
በወንድማማቾች መካከል ጠብ የሚዘራ ሰው።+
21 ምንጊዜም በልብህ አኑራቸው፤
በአንገትህም ዙሪያ እሰራቸው።
25 ውበቷን በልብህ አትመኝ፤+
የሚያማምሩ ዓይኖቿም አይማርኩህ፤
26 አንድ ሰው በዝሙት አዳሪ የተነሳ ለድህነት ይዳረጋልና፤*+
አመንዝራ ሴት ደግሞ የሰውን ውድ ሕይወት* ታጠምዳለች።
27 በጉያው እሳት ታቅፎ ልብሱ የማይቃጠልበት ሰው አለ?+
28 ወይስ በፍም ላይ ተራምዶ እግሮቹ የማይቃጠሉበት ሰው ይኖራል?
29 ከባልንጀራው ሚስት ጋር የሚተኛ ሰውም እንደዚሁ ነው፤
የሚነካት ሁሉ መቀጣቱ አይቀርም።+
30 ሌባ በተራበ ጊዜ ራሱን* ሊያጠግብ ቢሰርቅ፣
ሰዎች በንቀት አያዩትም።
31 በተያዘ ጊዜ ግን ሰባት እጥፍ ይከፍላል፤
በቤቱ ያለውን ውድ ነገር ሁሉ ያስረክባል።+
34 ቅናት ባልን እጅግ ያስቆጣዋልና፤
ለበቀል በሚነሳበት ጊዜም ፈጽሞ ርኅራኄ አያሳይም።+
35 ማንኛውንም ዓይነት ካሳ* አይቀበልም፤
ምንም ያህል ስጦታ ብታቀርብለት ቁጣው አይበርድም።