የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 17
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘዳግም የመጽሐፉ ይዘት

      • የሚቀርበው መሥዋዕት እንከን የለሽ መሆን አለበት (1)

      • ከሃዲዎችን በተመለከተ መደረግ ያለበት ነገር (2-7)

      • ለመዳኘት አስቸጋሪ የሆኑ የፍርድ ጉዳዮች (8-13)

      • ወደፊት ንጉሥ ቢያነግሡ መደረግ ያለበት ነገር (14-20)

        • ንጉሡ የሕጉን ቅጂ ለራሱ መገልበጥ ይኖርበታል (18)

ዘዳግም 17:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 22:20፤ ዘዳ 15:21፤ ሚል 1:8

ዘዳግም 17:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:23፤ 13:6-9

ዘዳግም 17:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:19
  • +ዘዳ 13:12-15

ዘዳግም 17:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 7:51

ዘዳግም 17:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 13:6, 10

ዘዳግም 17:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች አፍ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 18:16፤ ዮሐ 8:17፤ 1ጢሞ 5:19፤ ዕብ 10:28
  • +ዘኁ 35:30፤ ዘዳ 19:15

ዘዳግም 17:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 13:5፤ 1ቆሮ 5:13

ዘዳግም 17:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 35:11
  • +ዘዳ 12:5፤ 1ነገ 3:16, 28፤ መዝ 122:2, 5

ዘዳግም 17:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 7:15, 16
  • +ዘዳ 19:17፤ 21:5

ዘዳግም 17:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚል 2:7
  • +ዘዳ 5:32፤ 12:32

ዘዳግም 17:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 11:2፤ ዕብ 10:28
  • +ዘዳ 13:5፤ 1ቆሮ 5:13

ዘዳግም 17:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 13:11፤ 19:20

ዘዳግም 17:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 8:5, 20፤ 10:19

ዘዳግም 17:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 9:17፤ 10:24፤ 16:12, 13

ዘዳግም 17:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 20:1፤ 2ሳሙ 8:4፤ መዝ 20:7፤ ምሳሌ 21:31
  • +ኢሳ 31:1

ዘዳግም 17:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 11:1-3፤ ነህ 13:26
  • +ኢዮብ 31:24, 28፤ 1ጢሞ 6:9

ዘዳግም 17:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በጥቅልል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 31:9, 26፤ 2ነገ 22:8

ዘዳግም 17:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 1:2፤ 119:97
  • +2ዜና 34:18

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘዳ. 17:1ዘሌ 22:20፤ ዘዳ 15:21፤ ሚል 1:8
ዘዳ. 17:2ዘዳ 4:23፤ 13:6-9
ዘዳ. 17:3ዘዳ 4:19
ዘዳ. 17:3ዘዳ 13:12-15
ዘዳ. 17:4ዮሐ 7:51
ዘዳ. 17:5ዘዳ 13:6, 10
ዘዳ. 17:6ማቴ 18:16፤ ዮሐ 8:17፤ 1ጢሞ 5:19፤ ዕብ 10:28
ዘዳ. 17:6ዘኁ 35:30፤ ዘዳ 19:15
ዘዳ. 17:7ዘዳ 13:5፤ 1ቆሮ 5:13
ዘዳ. 17:8ዘኁ 35:11
ዘዳ. 17:8ዘዳ 12:5፤ 1ነገ 3:16, 28፤ መዝ 122:2, 5
ዘዳ. 17:91ሳሙ 7:15, 16
ዘዳ. 17:9ዘዳ 19:17፤ 21:5
ዘዳ. 17:11ሚል 2:7
ዘዳ. 17:11ዘዳ 5:32፤ 12:32
ዘዳ. 17:12ምሳሌ 11:2፤ ዕብ 10:28
ዘዳ. 17:12ዘዳ 13:5፤ 1ቆሮ 5:13
ዘዳ. 17:13ዘዳ 13:11፤ 19:20
ዘዳ. 17:141ሳሙ 8:5, 20፤ 10:19
ዘዳ. 17:151ሳሙ 9:17፤ 10:24፤ 16:12, 13
ዘዳ. 17:16ዘዳ 20:1፤ 2ሳሙ 8:4፤ መዝ 20:7፤ ምሳሌ 21:31
ዘዳ. 17:16ኢሳ 31:1
ዘዳ. 17:171ነገ 11:1-3፤ ነህ 13:26
ዘዳ. 17:17ኢዮብ 31:24, 28፤ 1ጢሞ 6:9
ዘዳ. 17:18ዘዳ 31:9, 26፤ 2ነገ 22:8
ዘዳ. 17:19መዝ 1:2፤ 119:97
ዘዳ. 17:192ዜና 34:18
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘዳግም 17:1-20

ዘዳግም

17 “እንከን ወይም ማንኛውም ዓይነት ጉድለት ያለበትን በሬ ወይም በግ ለአምላክህ ለይሖዋ አትሠዋ፤ ምክንያቱም ይህ ለአምላክህ ለይሖዋ አስጸያፊ ነው።+

2 “አምላክህ ይሖዋ ከሚሰጥህ ከተሞች በአንዱ ውስጥ በአምላክህ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር የሚፈጽምና ቃል ኪዳኑን የሚያፈርስ ወንድ ወይም ሴት ቢገኝ+ 3 እሱም ሄዶ ሌሎች አማልክትን በማምለክ እንዲሁም ለእነሱ ወይም ለፀሐይ አሊያም ለጨረቃ ወይም ደግሞ ለሰማይ ሠራዊት በሙሉ በመስገድ+ እኔ ያላዘዝኩትን ነገር ቢያደርግ+ 4 አንተም ይህ ነገር ቢነገርህ ወይም ሁኔታውን ብትሰማ ጉዳዩን በጥንቃቄ አጣራ። ይህ አስጸያፊ ነገር በእስራኤል ውስጥ መፈጸሙ እውነት እንደሆነ ቢረጋገጥ+ 5 እንዲህ ያለ መጥፎ ድርጊት የፈጸመውን ያንን ሰው ወይም ያቺን ሴት ወደ ከተማዋ በር አውጣቸው፤ ከዚያም ሰውየው ወይም ሴትየዋ እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ይወገሩ።+ 6 ሞት የሚገባው ሰው ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች በሚሰጡት ምሥክርነት*+ ይገደል። አንድ ምሥክር በሚሰጠው ቃል ብቻ መገደል የለበትም።+ 7 እሱን ለመግደል መጀመሪያ እጃቸውን የሚያነሱት ምሥክሮቹ መሆን ይኖርባቸዋል፤ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እጁን ያንሳበት። ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ።+

8 “ከከተሞችህ በአንዱ ውስጥ ለመዳኘት አስቸጋሪ የሆነ ክርክር ቢነሳ ለምሳሌ፣ ጉዳዩ ደም ማፍሰስን+ የሚመለከትም ይሁን ለሕግ አቤቱታ ማቅረብን ወይም የዓመፅ ድርጊትን አሊያም ሌሎች አለመግባባቶችን የሚመለከት ቢሆን ተነስተህ አምላክህ ይሖዋ ወደሚመርጠው ስፍራ ውጣ።+ 9 ወደ ሌዋውያን ካህናትና በዚያን ጊዜ ዳኛ ሆኖ ወደሚያገለግለው ሰው+ ሄደህ ጠይቅ፤ እነሱም ውሳኔውን ይነግሩሃል።+ 10 አንተም እነዚህ ሰዎች ይሖዋ በሚመርጠው ስፍራ ሆነው በነገሩህ ውሳኔ መሠረት እርምጃ ውሰድ። የሰጡህንም መመሪያ በሙሉ በጥንቃቄ ፈጽም። 11 በሚሰጡህ ሕግና በሚነግሩህ ውሳኔ መሠረት እርምጃ ውሰድ።+ እነሱ ካሳለፉት ውሳኔ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አትበል።+ 12 አምላክህን ይሖዋን የሚያገለግለውን ካህን ወይም ዳኛውን ባለመስማት እብሪተኛ የሚሆን ሰው ካለ ይገደል።+ ክፉ የሆነውን ከእስራኤል መካከል አስወግድ።+ 13 ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲሰማ ይፈራል፤ ከእንግዲህም የእብሪት ድርጊት አይፈጽምም።+

14 “አምላክህ ይሖዋ የሚሰጥህን ምድር ገብተህ ከወረስካት በኋላ በዚያ መኖር ስትጀምር ‘በዙሪያዬ እንዳሉት ብሔራት ሁሉ እኔም በላዬ ላይ ንጉሥ ላንግሥ’ ብትል+ 15 አምላክህ ይሖዋ የሚመርጠውን ንጉሥ ታነግሣለህ። የምታነግሠውም ንጉሥ ከወንድሞችህ መካከል መሆን ይኖርበታል።+ ወንድምህ ያልሆነን ባዕድ ሰው በላይህ ላይ ማንገሥ አይገባህም። 16 ይሁን እንጂ ንጉሡ ለራሱ ፈረሶች ማብዛት+ ወይም የፈረሶቹን ቁጥር ለመጨመር ሲል ሕዝቡ ወደ ግብፅ እንዲመለስ ማድረግ የለበትም፤+ ምክንያቱም ይሖዋ ‘በዚህ መንገድ ፈጽሞ ዳግመኛ እንዳትመለሱ’ ብሏችኋል። 17 ልቡ ከትክክለኛው መንገድ ዞር እንዳይል ለራሱ ሚስቶች አያብዛ፤+ ለራሱም ብርና ወርቅ አያከማች።+ 18 በመንግሥቱ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበትም ጊዜ በሌዋውያን ካህናት እጅ ካለው ላይ ወስዶ የዚህን ሕግ ቅጂ ለራሱ በመጽሐፍ* ላይ ይጻፍ።+

19 “አምላኩን ይሖዋን መፍራትን እንዲማር እንዲሁም በዚህ ሕግና በእነዚህ ሥርዓቶች ላይ የሰፈሩትን ቃላት በሙሉ በመፈጸም እንዲጠብቃቸው ይህ መጽሐፍ ከእሱ ጋር ይሁን፤+ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ያንብበው።+ 20 ይህን ካደረገ ልቡ በወንድሞቹ ላይ አይታበይም፤ ከትእዛዛቱም ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አይልም፤ ይህም እሱም ሆነ ልጆቹ በእስራኤል መካከል በመንግሥቱ ላይ ረጅም ዘመን እንዲቆዩ ያስችላቸዋል።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ