ኢሳይያስ
26 በዚያ ቀን በይሁዳ ምድር ይህ መዝሙር ይዘመራል፦+
“ጠንካራ ከተማ አለችን።+
እሱ መዳንን፣ ቅጥሯና መከላከያ ግንቧ ያደርጋል።+
2 ጻድቅ ብሔር ይኸውም በታማኝነት የሚመላለሰው ብሔር
እንዲገባ በሮቹን ክፈቱ።+
5 ከፍ ባለ ቦታ የሚኖሩትን፣
ከፍ ያለችውንም ከተማ ዝቅ አድርጓልና።
ያዋርዳታል፤ ወደ ምድር ይጥላታል፤
ከአፈርም ይደባልቃታል።
6 የጎስቋላ ሰው እግር፣
የችግረኞችም ኮቴ ይረግጣታል።”
7 የጻድቅ ሰው መንገድ ቀና* ነው።
አንተ ቅን ስለሆንክ
የጻድቁን መንገድ ደልዳላ ታደርጋለህ።
8 ይሖዋ ሆይ፣ የፍትሕ ጎዳናህን ስንከተል፣
ተስፋ የምናደርገው አንተን ነው።
9 ሁለንተናዬ* በሌሊት አንተን ለማግኘት ይጓጓል፤
አዎ፣ መንፈሴ አንተን በጥብቅ ትፈልጋለች፤+
በምድር ላይ በምትፈርድበት ጊዜ
የምድሪቱ ነዋሪዎች ስለ ጽድቅ+ ይማራሉና።
10 ክፉ ሰው ቸርነት ቢደረግለት እንኳ
ፈጽሞ ጽድቅን አይማርም።+
11 ይሖዋ ሆይ፣ እጅህ ከፍ ብሏል፤ እነሱ ግን አላዩትም።+
ለሕዝብህ ያለህን ቅንዓት በምታሳይበት ጊዜ ያያሉ፤ ለኀፍረትም ይዳረጋሉ።
አዎ፣ ለጠላቶችህ የተዘጋጀው እሳት ይበላቸዋል።
14 እነሱ ሞተዋል፤ በሕይወትም አይኖሩም።
በሞት ተረተዋል፤ አይነሱም።+
ታጠፋቸውና ስማቸው ጨርሶ እንዳይነሳ ታደርግ ዘንድ
ትኩረትህን ወደ እነሱ አዙረሃልና።
የምድሪቱን ወሰን ሁሉ እጅግ አሰፋህ።+
16 ይሖዋ ሆይ፣ በተጨነቁ ጊዜ አንተን ፈለጉ፤
በገሠጽካቸው ጊዜ በሹክሹክታ ድምፅ በመጸለይ ልባቸውን አፈሰሱ።+
17 ይሖዋ ሆይ፣ ነፍሰ ጡር ሴት ልትወልድ ስትል
ምጥ እንደሚይዛትና በምጥ ጣር እንደምትጮኽ ሁሉ
እኛም በአንተ የተነሳ እንዲሁ ሆነናል።
18 አርግዘን ነበር፤ ደግሞም አምጠን ነበር፤
ይሁንና ነፋስን የወለድን ያህል ነበር።
ለምድሪቱ መዳን አላስገኘንም
እንዲሁም በምድሪቱ ላይ እንዲኖር የተወለደ አንድም ልጅ የለም።
19 “ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ።
የእኔ አስከሬኖች ይነሳሉ።+
እናንተ በአፈር ውስጥ የምትኖሩ፣+
ተነሱ፤ በደስታም እልል በሉ!
20 ሕዝቤ ሆይ፣ ሂድ ወደ ውስጠኛው ክፍልህ ግባ፤
በርህንም ከኋላህ ዝጋ።+
21 እነሆ፣ ይሖዋ የምድሪቱ ነዋሪ የፈጸመውን በደል ለመፋረድ
ከመኖሪያ ቦታው ይመጣልና፤
ምድሪቱም በላይዋ የፈሰሰውን ደም ትገልጣለች፤
በላይዋም የተገደሉትን ከዚህ በኋላ አትደብቅም።”