መዝሙር
የዳዊት መዝሙር። ማስኪል።*
32 በደሉ ይቅር የተባለለት፣ ኃጢአቱ የተሸፈነለት* ሰው+ ደስተኛ ነው።
2 ይሖዋ በጥፋተኝነት የማይጠይቀው፣
በመንፈሱ ሽንገላ የሌለበት ሰው ደስተኛ ነው።+
3 ዝም ባልኩ ጊዜ፣ ቀኑን ሙሉ ከመቃተቴ የተነሳ አጥንቶቼ መነመኑ።+
4 ቀንና ሌሊት እጅህ* በእኔ ላይ ከብዳለችና።+
በበጋ ንዳድ እንደሚተን ውኃ ኃይሌ ተነነ።* (ሴላ)
5 በመጨረሻ ኃጢአቴን ለአንተ ተናዘዝኩ፤
ስህተቴን አልሸፋፈንኩም።+
“የፈጸምኳቸውን በደሎች ለይሖዋ እናዘዛለሁ” አልኩ።+
አንተም ስህተቴንና ኃጢአቴን ይቅር አልክ።+ (ሴላ)
6 ታማኝ የሆነ ሁሉ
አንተ በምትገኝበት ጊዜ ወደ አንተ የሚጸልየው ለዚህ ነው።+
በዚህ ጊዜ ኃይለኛ ጎርፍ እንኳ አይነካውም።
7 አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤
ከጭንቀት ትሰውረኛለህ።+
8 አንተ እንዲህ ብለሃል፦ “ጥልቅ ማስተዋል እሰጥሃለሁ፤ ልትሄድበት የሚገባውንም መንገድ አስተምርሃለሁ።+
ዓይኔን በአንተ ላይ አድርጌ እመክርሃለሁ።+
10 የክፉ ሰው ሥቃይ ብዙ ነው፤
በይሖዋ የሚታመን ሰው ግን ታማኝ ፍቅሩ ይከበዋል።+
11 ጻድቃን ሆይ፣ በይሖዋ ደስ ይበላችሁ፤ ሐሴትም አድርጉ፤
ልበ ቀና የሆናችሁ ሁሉ፣ እልል በሉ።