መዝሙር
ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ።+
4 መላእክቱን መናፍስት፣
አገልጋዮቹን የሚባላ እሳት ያደርጋል።+
6 ጥልቅ ውኃን እንደ ልብስ አለበስካት።+
ውኃዎቹ ከተራሮቹ በላይ ቆሙ።
7 በገሠጽካቸው ጊዜ ሸሹ፤+
የነጎድጓድህን ድምፅ ሲሰሙ በድንጋጤ ፈረጠጡ፤
8 ተራሮች ወደ ላይ ወጡ፤+ ሸለቆዎችም ወደ ታች ወረዱ፤
ሁሉም ወዳዘጋጀህላቸው ቦታ ሄዱ።
9 ውኃዎቹ አልፈው እንዳይሄዱ፣
እንደገናም ምድርን እንዳይሸፍኑ ወሰን አበጀህላቸው።+
10 ምንጮችን ወደ ሸለቆዎች* ይልካል፤
በተራሮች መካከል ይፈስሳሉ።
11 የዱር አራዊት ሁሉ ከዚያ ይጠጣሉ፤
የዱር አህዮችም ጥማቸውን ይቆርጣሉ።
12 የሰማይ ወፎች ከእነሱ በላይ ይሰፍራሉ፤
በለመለሙ የዛፍ ቅርንጫፎች መካከል ሆነው ይዘምራሉ።
13 ከላይ ካሉት ክፍሎቹ ሆኖ ተራሮችን ያጠጣል።+
በሥራህ ፍሬ ምድር ረካች።+
14 ሣርን ለከብት፣
አትክልትንም ለሰው ልጆች ጥቅም ያበቅላል፤+
ይህን የሚያደርገው ምድር እህል እንድታስገኝ ነው፤
15 እንዲሁም የሰውን ልብ ደስ የሚያሰኝ የወይን ጠጅ፣+
ፊትን የሚያበራ ዘይትና
የሰውን ልብ የሚያበረታ እህል እንዲገኝ ነው።+
16 የይሖዋ ዛፎች፣ እሱ የተከላቸው አርዘ ሊባኖሶች፣
ውኃ ጠጥተው ይረካሉ፤
17 በዚያ ወፎች ጎጇቸውን ይሠራሉ።
19 ጊዜያትን ለመለየት ጨረቃን ሠራ፤
ፀሐይ የምትጠልቅበትን ጊዜ በሚገባ ታውቃለች።+
20 ጨለማን ታመጣለህ፤ ሌሊትም ይሆናል፤+
በዚህ ጊዜ በጫካ የሚኖሩ አራዊት ሁሉ ወጥተው ይንቀሳቀሳሉ።
22 ፀሐይ ስትወጣ፣
ተመልሰው በየጎሬአቸው ይተኛሉ።
23 ሰውም ወደ ሥራው ተሰማርቶ
እስኪመሽ ድረስ ሲሠራ ይውላል።
24 ይሖዋ ሆይ፣ ሥራህ ምንኛ ብዙ ነው!+
ሁሉንም በጥበብ ሠራህ።+
ምድር በፈጠርካቸው ነገሮች ተሞልታለች።
25 ባሕሩ እጅግ ትልቅና ሰፊ ነው፤
በዚያ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ትናንሽም ሆኑ ትላልቅ ሕያዋን ነገሮች ይርመሰመሳሉ።+
27 በወቅቱ ምግባቸውን እንድትሰጣቸው፣
ሁሉም አንተን ይጠባበቃሉ።+
28 አንተ የምትሰጣቸውን ይሰበስባሉ።+
እጅህን ስትከፍት መልካም ነገሮችን ይጠግባሉ።+
29 ፊትህን ስትሰውር ይታወካሉ።
መንፈሳቸውን ከወሰድክ ይሞታሉ፤ ወደ አፈርም ይመለሳሉ።+
30 መንፈስህን ከላክ ይፈጠራሉ፤+
የምድርንም ገጽ ታድሳለህ።
31 የይሖዋ ክብር ለዘላለም ይኖራል።
ይሖዋ በሥራው ሐሴት ያደርጋል።+
32 ምድርን ሲመለከት ትንቀጠቀጣለች፤
ተራሮችን ሲነካ ይጨሳሉ።+
34 ሐሳቤ እሱን የሚያስደስት ይሁን።*
እኔም በይሖዋ ሐሴት አደርጋለሁ።
35 ኃጢአተኞች ከምድር ይጠፋሉ፤
ክፉዎችም ከእንግዲህ አይገኙም።+