ኢሳይያስ
25 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ አምላኬ ነህ።
2 ከተማዋን የድንጋይ ቁልል፣
የተመሸገችውንም ከተማ የፍርስራሽ ክምር አድርገሃልና።
የባዕዳኑ ማማ፣ ከተማ መሆኑ አብቅቶለታል፤
ከተማዋ በምንም ዓይነት ዳግመኛ አትገነባም።
3 ከዚህም የተነሳ ኃያል የሆነ ሕዝብ ያከብርሃል፤
የጨቋኝ ብሔራት ከተማም ትፈራሃለች።+
የጨቋኞች ቁጣ ከግንብ ጋር እንደሚላተም ውሽንፍር በሚሆንበት ጊዜ ጥበቃ ታደርጋለህ፤
5 ውኃ በተጠማ ምድር እንዳለ ሙቀት
የባዕዳንን ሁከት ጸጥ ታደርጋለህ።
በደመና ጥላ እንደሚበርድ ሙቀት፣
የጨቋኞችም ዝማሬ ጸጥ ረጭ ይላል።
6 የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በዚህ ተራራ+ ላይ ለሕዝቦች ሁሉ
ምርጥ ምግቦች* የሚገኙበት ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል፤+
ያረጀ የወይን ጠጅ ግብዣ፣
መቅኒ የሞላባቸው ምርጥ ምግቦች
እንዲሁም የተጣራና ጥሩ የወይን ጠጅ የሚቀርቡበት ታላቅ ግብዣ ያደርጋል።
7 በዚህ ተራራ ላይ ሕዝቦችን ሁሉ የሸፈነውን ከፈን
እንዲሁም ብሔራትን ሁሉ ተብትቦ የያዘውን መሸፈኛ ያስወግዳል።*
በሕዝቡ ላይ የደረሰውን ነቀፋ ከመላው ምድር ያስወግዳል፤
ይሖዋ ራሱ ይህን ተናግሯልና።
9 በዚያም ቀን እንዲህ ይላሉ፦
“እነሆ፣ አምላካችን ይህ ነው!+
ይሖዋ ይህ ነው!
እሱን ተስፋ አድርገናል።
በእሱ ማዳን ደስ ይበለን፤ ሐሴትም እናድርግ።”+
12 የተመሸገውን ከተማ
ከረጃጅም የመከላከያ ግንቦችህ ጋር ያፈርሳል፤
ምድር ላይ ጥሎ ከአፈር ይደባልቀዋል።