መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት መዝሙር። ማህሌት።
139 ይሖዋ ሆይ፣ በሚገባ መርምረኸኛል፤ ደግሞም ታውቀኛለህ።+
2 አንተ ስቀመጥም ሆነ ስነሳ ታውቃለህ።+
ሐሳቤን ከሩቅ ታስተውላለህ።+
3 ስጓዝም ሆነ ስተኛ በሚገባ ታየኛለህ፤
መንገዶቼን ሁሉ ታውቃለህ።+
4 ይሖዋ ሆይ፣ ገና ቃል ከአፌ ሳይወጣ፣
እነሆ፣ አንተ ሁሉን ነገር አስቀድመህ በሚገባ ታውቃለህ።+
5 ከኋላም ከፊትም ከበብከኝ፤
እጅህንም በላዬ ላይ ታደርጋለህ።
6 እንዲህ ያለው እውቀት እኔ ልረዳው ከምችለው በላይ ነው።*
በጣም ከፍ ያለ ከመሆኑ የተነሳ ልደርስበት አልችልም።*+
7 ከመንፈስህ ወዴት ላመልጥ እችላለሁ?
ከፊትህስ ወዴት ልሸሽ እችላለሁ?+
11 “በእርግጥ ጨለማ ይሰውረኛል!” ብል፣
በዚያን ጊዜ በዙሪያዬ ያለው ሌሊት ብርሃን ይሆናል።
14 በሚያስደምም ሁኔታ ግሩምና ድንቅ ሆኜ ስለተፈጠርኩ+ አወድስሃለሁ።
16 ፅንስ እያለሁ እንኳ ዓይኖችህ አዩኝ፤
የአካሌ ክፍሎች በሙሉ በመጽሐፍህ ተጻፉ፤
አንዳቸውም ወደ ሕልውና ከመምጣታቸው በፊት፣
የተሠሩባቸውን ቀኖች በተመለከተ በዝርዝር ተጻፈ።
17 ሐሳቦችህ ለእኔ ምንኛ ውድ ናቸው!+
አምላክ ሆይ፣ ቁጥራቸው ምንኛ ብዙ ነው!+
18 ልቆጥራቸው ብሞክር ከአሸዋ ይልቅ ይበዛሉ።+
19 አምላክ ሆይ፣ ምነው ክፉውን በገደልከው!+
22 እጅግ ጠላኋቸው፤+
ለእኔ የለየላቸው ጠላቶች ሆነዋል።
23 አምላክ ሆይ፣ በሚገባ ፈትሸኝ፤ ልቤንም እወቅ።+