ናሆም
1 በነነዌ ላይ የተላለፈ ፍርድ፦+ የኤልቆሻዊው የናሆም* የራእዩ መጽሐፍ ይህ ነው፦
ይሖዋ ባላጋራዎቹን ይበቀላል፤
ለጠላቶቹም ቁጣ ያከማቻል።
መንገዱ በአደገኛ ነፋስና በወጀብ ውስጥ ነው፤
ደመናት ከእግሩ በታች እንዳለ አቧራ ናቸው።+
ባሳንና ቀርሜሎስ ይጠወልጋሉ፤+
የሊባኖስ አበባዎችም ይጠወልጋሉ።
5 ከእሱ የተነሳ ተራሮች ይንቀጠቀጣሉ፤
ኮረብቶችም ይቀልጣሉ።+
ከፊቱም የተነሳ ምድር፣
የብስና በላዩ የሚኖሩት ሁሉ ይናወጣሉ።+
6 በቁጣው ፊት ማን ሊቆም ይችላል?+
የንዴቱን ትኩሳት ሊቋቋም የሚችልስ ማን ነው?+
ቁጣው እንደ እሳት ይፈስሳል፤
ዓለቶችም ከእሱ የተነሳ ይፈረካከሳሉ።
7 ይሖዋ ጥሩ ነው፤+ በጭንቀትም ቀን መሸሸጊያ ነው።+
8 ጠራርጎ በሚወስድ ጎርፍ ስፍራዋን* ፈጽሞ ያጠፋል፤
ጠላቶቹንም ጨለማ ያሳድዳቸዋል።
9 በይሖዋ ላይ የምታሴሩት ምንድን ነው?
እሱ ፈጽሞ ያጠፋል።
ጭንቀት ዳግመኛ አይመጣም።+
11 በይሖዋ ላይ ክፉ ነገር የሚያሴር፣
ከንቱ ምክርም የሚሰጥ ከመካከልሽ ይወጣል።
12 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“ምንም እንኳ የተሟላ ኃይል ያላቸውና ብዙዎች ቢሆኑም
ይቆረጣሉ፤ ደግሞም ይጠፋሉ።*
መከራ አሳይቼሃለሁ፤* ከዚያ በኋላ ግን መከራ አላመጣብህም።
13 አሁንም ቀንበሩን ከአንተ ላይ እሰብራለሁ፤+
እስራትህንም እበጥሳለሁ።
14 ይሖዋ አንተን* በተመለከተ እንዲህ ሲል አዟል፦
‘ከእንግዲህ ስምህን የሚያስጠራ አይኖርም።
የተቀረጹትን ምስሎችና ከብረት የተሠሩትን ሐውልቶች* ከአማልክትህ ቤት* አስወግዳለሁ።
የተናቅክ ስለሆንክ መቃብር አዘጋጅልሃለሁ።’
15 እነሆ ምሥራች ይዞ የሚመጣ፣
ሰላምንም የሚያውጅ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው።+
ይሁዳ ሆይ፣ በዓሎችሽን አክብሪ፤+ ስእለትሽን ፈጽሚ፤
ከእንግዲህ ወዲህ የማይረባ ሰው በመካከልሽ አያልፍምና።
እንዲህ ያለው ሰው ሙሉ በሙሉ ይወገዳል።”
ምሽጎቹን ጠብቂ።
መንገዱን በትኩረት ተመልከቺ።
ወገብሽን ታጠቂ፤* ኃይልሽንም ሁሉ አሰባስቢ።
3 የኃያላኑ ጋሻዎች ቀይ ቀለም የተነከሩ ናቸው፤
ተዋጊዎቹ ደማቅ ቀይ ልብስ ለብሰዋል።
ለጦርነት ዝግጁ በሚሆንበት ቀን፣
የጦር ሠረገላው ብረቶች እንደ እሳት ያብረቀርቃሉ፤
ከጥድ የተሠሩት ረጃጅም ጦሮች ይወዛወዛሉ።
4 የጦር ሠረገሎቹ በጎዳናዎቹ ላይ ይከንፋሉ።
በአደባባዮቹም ላይ ወዲያ ወዲህ ይራወጣሉ።
እንደሚነድ ችቦ ያበራሉ፤ እንደ መብረቅም ያንጸባርቃሉ።
5 እሱ አለቆቹን ይጠራል።
እነሱ ወደ ፊት ሲገሰግሱ ይሰናከላሉ።
ወደ ቅጥሯ እየተጣደፉ ይሄዳሉ፤
መከላከያም ያቆማሉ።
6 የወንዞቹ በሮች ይከፈታሉ፤
ቤተ መንግሥቱም ይቀልጣል።*
8 ነነዌ ከተቆረቆረችበት+ ጊዜ አንስቶ እንደ ውኃ ኩሬ ነበረች፤
አሁን ግን እነሱ ይሸሻሉ።
አንዳንዶች “ቁሙ! ቁሙ!” ብለው ይጮኻሉ።
ሆኖም ወደ ኋላ የሚዞር የለም።+
9 ብሩን ዝረፉ፤ ወርቁን ዝረፉ!
የተከማቸው ሀብት ስፍር ቁጥር የለውም።
በብዙ ዓይነት የከበሩ ዕቃዎች ተሞልቷል።
10 ከተማዋ ባዶና ወና እንዲሁም ባድማ ሆናለች!+
ልባቸው በፍርሃት ቀልጧል፤ ጉልበታቸው ተብረክርኳል፤ ወገባቸውም ተንቀጥቅጧል፤
የሁሉም ፊት ቀልቷል።
12 አንበሳው ለግልገሎቹ የሚበቃቸውን ያህል አደነ፤
ለእንስቶቹም አንቆ ገደለላቸው።
ጎሬውን በታደኑ እንስሶች፣
ዋሻውንም በተቦጫጨቁ እንስሶች ሞላ።
አደንሽን ከምድር ገጽ አስወግዳለሁ፤
የመልእክተኞችሽም ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ አይሰማም።”+
3 ለደም አፍሳሿ ከተማ ወዮላት!
በማታለልና በዝርፊያ የተሞላች ናት።
ከማደን ቦዝና አታውቅም!
2 የአለንጋ ድምፅና የመንኮራኩር* ኳኳቴ ይሰማል፤
ፈረሶች ሲጋልቡና ሠረገሎች ሲፈተለኩ ይታያል።
3 ፈረስ ጋላቢው ይጋልባል፤ ሰይፉ ያንጸባርቃል፤ ጦሩ ያብረቀርቃል፤
የተገደሉት በጣም ብዙ ናቸው፤ የአስከሬን ክምር ይታያል፤
ሬሳው ስፍር ቁጥር የለውም።
አስከሬኖቹም ያደናቅፏቸዋል።
4 ይህ የሆነው ዝሙት አዳሪዋ በምትፈጽመው በርካታ የአመንዝራነት ተግባር የተነሳ ነው፤
እሷ ብሔራትን በምንዝሯ፣ ወገኖችንም በጥንቆላዋ የምታጠምድ፣
የምታምርና የምትማርክ እንዲሁም በጥንቆላ የተካነች ናት።
5 “እነሆ፣ በአንቺ* ላይ ተነስቻለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤+
“ቀሚስሽን እስከ ፊትሽ ድረስ እገልበዋለሁ፤
ብሔራትም እርቃንሽን፣
መንግሥታትም ነውርሽን እንዲያዩ አደርጋለሁ።
7 አንቺን የሚያይ ሁሉ ከአንቺ ይሸሻል፤+
ደግሞም ‘ነነዌ ወድማለች!
የሚያዝንላት ማን ነው?’ ይላል።
አንቺን የሚያጽናና ከየት ማግኘት እችላለሁ?
8 አንቺ በአባይ የመስኖ ቦዮች+ አጠገብ ከነበረችው ከኖአሞን*+ ትሻያለሽ?
እሷ በውኃ የተከበበች ነበረች፤
ባሕሩም ሀብት ያስገኝላት፣ እንደ ቅጥርም ሆኖ ያገለግላት ነበር።
9 ኢትዮጵያና ግብፅ ገደብ የለሽ የኃይል ምንጮቿ ነበሩ።
10 ይሁንና እሷም እንኳ በግዞት ተወሰደች፤
ተማርካም ሄደች።+
ልጆቿም በየመንገዱ ማዕዘን* ተፈጠፈጡ።
በተከበሩ ሰዎቿ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፤
ታላላቅ ሰዎቿም ሁሉ በእግር ብረት ታሰሩ።
11 አንቺም ትሰክሪያለሽ፤+
ደግሞም ትሰወሪያለሽ።
ከጠላት የምትሸሸጊበት ቦታ ትፈልጊያለሽ።
12 ምሽጎችሽ ሁሉ የመጀመሪያዎቹን የበሰሉ ፍሬዎች እንደያዙ የበለስ ዛፎች ናቸው፤
ዛፎቹ ከተነቀነቁ ፍሬዎቹ ረግፈው በበላተኛ አፍ ውስጥ ይወድቃሉ።
13 እነሆ፣ ወታደሮችሽ በመካከልሽ እንዳሉ ሴቶች ናቸው።
የምድርሽ በሮች ለጠላቶችሽ ወለል ብለው ይከፈታሉ።
የበሮችሽን መቀርቀሪያዎች እሳት ይበላቸዋል።
14 ለከበባው ውኃ ቅጂ!+
ምሽጎችሽን አጠናክሪ።
ማጥ ውስጥ ግቢ፤ ጭቃውንም ርገጪ፤
የጡብ ቅርጽ ማውጫውንም ያዢ።
15 ይህም ሆኖ እሳት ይበላሻል።
ሰይፍ ይቆርጥሻል።+
እንደ ኩብኩባ ይበላሻል።+
እንደ ኩብኩባ ተባዢ!
አዎ፣ እንደ አንበጣ ተራቢ!
16 ነጋዴዎችሽን ከሰማያት ከዋክብት ይበልጥ አብዝተሻል።
ኩብኩባው ቅርፊቱን ከላዩ ላይ ጥሎ ይበርራል።
17 ጠባቂዎችሽ እንደ አንበጣ፣
መኮንኖችሽም እንደ አንበጣ መንጋ ናቸው።
ቅዝቃዜ ባለበት ቀን በድንጋይ ቅጥሮች ውስጥ ይሰፍራሉ፤
ፀሐይ ስትወጣ ግን በርረው ይሄዳሉ፤
የት እንደደረሱም ማንም አያውቅም።
18 የአሦር ንጉሥ ሆይ፣ እረኞችህ እንቅልፍ ተጫጭኗቸዋል፤
ታላላቅ ሰዎችህ በመኖሪያቸው ይቀመጣሉ።
ሕዝብህ በተራሮቹ ላይ ተበታትነዋል፤
የሚሰበስባቸውም የለም።+
19 የደረሰብህን መቅሰፍት የሚያቆም ነገር የለም።
ቁስልህ ሊድን የሚችል አይደለም።
“አጽናኝ” የሚል ትርጉም አለው።
ወይም “ይንከባከባል።”
ነነዌን ያመለክታል።
ወይም “ከስንዴ የሚዘጋጅ መጠጥ።”
“እሱም በመካከላቸው ያልፋል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ይሁዳን ያመለክታል።
አሦርን ያመለክታል።
ወይም “ቀልጠው የተሠሩትን ሐውልቶች።”
ወይም “ቤተ መቅደስ።”
ነነዌን ያመለክታል።
ቃል በቃል “ዳሌዎችሽን አጠንክሪ።”
ወይም “ይፈርሳል።”
ወይም “ተቆርጧል።”
ቃል በቃል “ልባቸውን።”
ተሽከርካሪ እግር።
ነነዌን ያመለክታል።
ቴብስን ያመለክታል።
ቃል በቃል “በጎዳናዎች ሁሉ ራስ ላይ።”