የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • nwt 2 ተሰሎንቄ 1:1-3:18
  • 2 ተሰሎንቄ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 2 ተሰሎንቄ
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ተሰሎንቄ

ለተሰሎንቄ ሰዎች የተጻፈ ሁለተኛው ደብዳቤ

1 አባታችን ከሆነው አምላክና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድነት ላለው የተሰሎንቄ ሰዎች ጉባኤ፣ ከጳውሎስ፣ ከስልዋኖስና* ከጢሞቴዎስ+ የተላከ ደብዳቤ፦

2 አባት ከሆነው አምላክና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

3 ወንድሞች፣ ስለ እናንተ አምላክን ሁልጊዜ ለማመስገን እንገፋፋለን። እምነታችሁ እጅግ እያደገ በመሄዱና ሁላችሁም እርስ በርስ የምታሳዩት ፍቅር እየጨመረ በመምጣቱ ይህን ማድረጋችን ተገቢ ነው።+ 4 ስለዚህ እየደረሰባችሁ* ያለውን ስደትና መከራ ሁሉ ችላችሁ በመኖር+ ባሳያችሁት ጽናትና እምነት የተነሳ በአምላክ ጉባኤዎች መካከል እኛ ራሳችን ስለ እናንተ በኩራት እንናገራለን።+ 5 ይህ ሁሉ አምላክ ትክክለኛ ፍርድ እንደፈረደ የሚያሳይ ማስረጃ ከመሆኑም በተጨማሪ መከራ እየተቀበላችሁለት ላለው የአምላክ መንግሥት ብቁ ሆናችሁ እንድትቆጠሩ የሚያደርግ ነው።+

6 ከዚህ አንጻር አምላክ መከራን ለሚያመጡባችሁ በአጸፋው መከራን መክፈሉ የጽድቅ እርምጃ ነው።+ 7 መከራን የምትቀበሉት እናንተ ግን ጌታ ኢየሱስ ከኃያላን መላእክቱ ጋር+ ከሰማይ በሚገለጥበት ጊዜ+ ከእኛ ጋር እረፍት ይሰጣችኋል፤ 8 የሚገለጠውም በሚንበለበል እሳት ነው፤ በዚያን ጊዜ አምላክን በማያውቁትና ስለ ጌታችን ኢየሱስ ለሚገልጸው ምሥራች በማይታዘዙት ላይ የበቀል እርምጃ ይወስዳል።+ 9 እነዚህ ሰዎች ዘላለማዊ ጥፋት ተፈርዶባቸው ከጌታ ፊት ይወገዳሉ፤+ ክብራማ ኃይሉንም አያዩም፤ 10 በዚያን ጊዜ ከቅዱሳኑ ጋር ሊከበር ይመጣል፤ በእሱ የሚያምኑም ሁሉ በአድናቆት ያዩታል፤ እናንተም የሰጠናችሁን ምሥክርነት በእምነት ስለተቀበላችሁ ከእነሱ መካከል ትቆጠራላችሁ።

11 በዚህ ምክንያት አምላካችን ለጥሪው+ ብቁዎች አድርጎ እንዲቆጥራችሁ እንዲሁም የወደደውን መልካም ነገር ሁሉና በእምነት ተገፋፍታችሁ የምታከናውኑትን ሥራ በኃይሉ አማካኝነት ሙሉ በሙሉ እንዲፈጽም ስለ እናንተ ሁልጊዜ እንጸልያለን። 12 ይህም በአምላካችንና በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ መሠረት የጌታችን የኢየሱስ ስም በእናንተ እንዲከበርና እናንተም ከእሱ ጋር ባላችሁ አንድነት እንድትከበሩ ነው።

2 ይሁን እንጂ ወንድሞች፣ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገኘትና+ ከእሱ ጋር ለመሆን አንድ ላይ መሰብሰባችንን+ በተመለከተ ይህን እንለምናችኋለን፤ 2 በመንፈስ በተነገረ ቃል* ወይም በቃል መልእክት ወይም ደግሞ ከእኛ የተላከ በሚመስል ደብዳቤ አማካኝነት የይሖዋ* ቀን+ ደርሷል ብላችሁ በማሰብ የማመዛዘን ችሎታችሁ በቀላሉ አይናወጥ፤+ ደግሞም አትደናገጡ።

3 ማንም ሰው በምንም መንገድ አያሳስታችሁ፤ ምክንያቱም በመጀመሪያ ክህደቱ+ ሳይመጣና የጥፋት ልጅ የሆነው የዓመፅ ሰው+ ሳይገለጥ ያ ቀን አይመጣም።+ 4 እሱ አምላክ ነኝ እያለ በማወጅ በአምላክ ቤተ መቅደስ ይቀመጥ ዘንድ አምላክ ተብሎ ከሚጠራ ወይም ከሚመለክ ነገር ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ተቃዋሚ ነው። 5 ያኔ ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ እነዚህን ነገሮች እነግራችሁ እንደነበር አታስታውሱም?

6 በገዛ ራሱ ጊዜ ይገለጥ ዘንድ አሁን የሚያግደው ነገር ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ። 7 እርግጥ ሚስጥራዊ የሆነው ይህ ዓመፅ አሁንም እየሠራ ነው፤+ ሆኖም ሚስጥር ሆኖ የሚቆየው አሁን አግዶት ያለው ነገር ከመንገድ እስኪወገድ ድረስ ብቻ ነው። 8 ከዚያ በኋላ ጌታ ኢየሱስ በአፉ መንፈስ+ የሚያስወግደውና የእሱ መገኘት ይፋ በሚሆንበት ጊዜ+ እንዳልነበረ የሚያደርገው ዓመፀኛ ይገለጣል። 9 ሆኖም የዓመፀኛው መገኘት የሰይጣን ሥራ+ ሲሆን ይህም የሚፈጸመው በተአምራት፣ በሐሰተኛ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች ሁሉ+ 10 እንዲሁም ለማታለል ማንኛውንም ዓይነት የክፋት ዘዴ+ በመጠቀም ነው። ወደ ጥፋት እያመሩ ያሉት ሰዎች ይድኑ ዘንድ የእውነት ፍቅር በውስጣቸው ስለሌለ ይህ ሁሉ እንደ ቅጣት ይደርስባቸዋል። 11 በዚህም ምክንያት አምላክ ሐሰት የሆነውን ያምኑ ዘንድ አታላይ በሆነ ተጽዕኖ ተሸንፈው እንዲስቱ ይፈቅዳል፤+ 12 ይህን የሚያደርገው እውነትን ከማመን ይልቅ በዓመፅ ስለሚደሰቱ ሁሉም እንዲፈረድባቸው ነው።

13 ይሁን እንጂ በይሖዋ* የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ አምላክ እናንተን በመንፈሱ በመቀደስ+ እንዲሁም በእውነት ላይ ባላችሁ እምነት መዳን እንድታገኙ ከመጀመሪያው አንስቶ ስለመረጣችሁ+ አምላክን ስለ እናንተ ሁልጊዜ ለማመስገን እንገፋፋለን። 14 የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር እንድታገኙ፣ እኛ በምናውጀው ምሥራች አማካኝነት ለዚህ ዓላማ ጠርቷችኋል።+ 15 ስለዚህ ወንድሞች ጸንታችሁ ቁሙ፤+ እንዲሁም ከእኛ በተላከ የቃል መልእክትም ሆነ ደብዳቤ የተማራችኋቸውን ወጎች አጥብቃችሁ ያዙ።+ 16 በተጨማሪም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እንዲሁም የወደደን፣+ በጸጋም አማካኝነት ዘላለማዊ መጽናኛና መልካም ተስፋ+ የሰጠን አባታችን የሆነው አምላክ 17 ልባችሁን ያጽናኑ፤ እንዲሁም ምንጊዜም መልካም የሆነውን ነገር እንድታደርጉና እንድትናገሩ ያጽኗችሁ።*

3 በመጨረሻም ወንድሞች፣ በእናንተ ዘንድ እንደሆነው ሁሉ የይሖዋ* ቃል በፍጥነት መስፋፋቱን እንዲቀጥልና+ እንዲከበር ስለ እኛ መጸለያችሁን አታቋርጡ፤+ 2 ደግሞም ከመጥፎና ከክፉ ሰዎች እንድንድን+ ጸልዩልን፤ እምነት ሁሉም ሰው የሚኖረው ነገር አይደለምና።+ 3 ጌታ ግን ታማኝ ነው፤ እሱ ያጠነክራችኋል፤ እንዲሁም ከክፉው ይጠብቃችኋል። 4 ከዚህም በላይ እኛ የጌታ ተከታዮች እንደመሆናችን መጠን፣ ያዘዝናችሁን እያደረጋችሁ እንዳለና ወደፊትም ማድረጋችሁን እንደምትቀጥሉ በእናንተ እንተማመናለን። 5 አምላክን እንድትወዱና+ ክርስቶስን በጽናት+ እንድትከተሉ ጌታ ልባችሁን በትክክለኛው አቅጣጫ መምራቱን ይቀጥል።

6 ወንድሞች፣ በሥርዓት ከማይሄድና+ ከእኛ የተቀበላችሁትን* ወግ* ከማይከተል+ ማንኛውም ወንድም እንድትርቁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን። 7 የእኛን አርዓያ እንዴት መከተል እንዳለባችሁ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ፤+ ምክንያቱም በመካከላችሁ ሳለን ሥርዓት በጎደለው መንገድ አልተመላለስንም፤ 8 እንዲሁም የማንንም ምግብ በነፃ አልበላንም።+ እንዲያውም ብዙ ወጪ በማስወጣት በማናችሁም ላይ ሸክም ላለመሆን ሌት ተቀን በመሥራት እንደክምና እንለፋ ነበር።+ 9 ይህን ያደረግነው የእኛን አርዓያ እንድትከተሉ+ ራሳችንን ለእናንተ ምሳሌ አድርገን ለማቅረብ ብለን እንጂ ሥልጣን ሳይኖረን ቀርቶ አይደለም።+ 10 እንዲያውም ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ “መሥራት የማይፈልግ ሁሉ አይብላ” የሚል ትእዛዝ ሰጥተናችሁ ነበር።+ 11 አንዳንዶች ሥራ ፈት በመሆን በማይመለከታቸው ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ+ ሥርዓት በጎደለው መንገድ በመካከላችሁ እንደሚመላለሱ እንሰማለንና።+ 12 እንዲህ ያሉ ሰዎች አርፈው ሥራቸውን በመሥራት በድካማቸው ያገኙትን እንዲበሉ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛቸዋለን፤ እንዲሁም አጥብቀን እንመክራቸዋለን።+

13 እናንተ ግን ወንድሞች፣ መልካም የሆነውን ከማድረግ አትታክቱ። 14 ሆኖም በዚህ ደብዳቤ አማካኝነት ላስተላለፍነው ቃል የማይታዘዝ ሰው ቢኖር ይህን ሰው ምልክት አድርጉበት፤* ያፍርም ዘንድ ከእሱ ጋር አትግጠሙ።+ 15 ይሁን እንጂ እንደ ጠላት አትመልከቱት፤ ከዚህ ይልቅ እንደ ወንድም አጥብቃችሁ መምከራችሁን ቀጥሉ።+

16 የሰላም ጌታ ራሱ በሁሉም መንገድ ዘወትር ሰላም ይስጣችሁ።+ ጌታ ከሁላችሁም ጋር ይሁን።

17 እኔ ጳውሎስ በገዛ እጄ የጻፍኩላችሁ ሰላምታ ይድረሳችሁ፤+ ይህ የእጅ ጽሑፍ የደብዳቤዎቼ ሁሉ መለያ ነው፤ አጻጻፌ እንዲህ ነው።

18 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችሁም ጋር ይሁን።

ሲላስ ተብሎም ይጠራል።

ወይም “በጽናት እያሳለፋችሁት።”

የቃላት መፍቻው ላይ “መንፈስ” የሚለውን ተመልከት።

ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

ወይም “ያበርቷችሁ።”

ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

“ከእኛ የተቀበሉትን” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ወይም “መመሪያ፤ ትምህርት።”

ወይም “በትኩረት ተከታተሉት።”

    የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ