የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 2:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  4 እሱ በብሔራት መካከል ይፈርዳል፤

      ከብዙ ሕዝቦች ጋር በተያያዘም ሁሉንም ነገር ያቀናል።*

      እነሱ ሰይፋቸውን ማረሻ፣

      ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ።+

      አንዱ ብሔር በሌላው ብሔር ላይ ሰይፍ አያነሳም፤

      ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይማሩም።+

  • ኢሳይያስ 35:9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  9 በዚያ አንበሳ አይኖርም፤

      አዳኝ አራዊትም ወደዚያ አይወጡም።

      አንዳቸውም በዚያ አይገኙም፤+

      የተቤዡት ብቻ በዚያ ይሄዳሉ።+

  • ኢሳይያስ 51:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  3 ይሖዋ ጽዮንን ያጽናናታልና።+

      ፍርስራሾቿን ሁሉ ያጽናናል፤+

      ምድረ በዳዋንም እንደ ኤደን፣+

      በረሃማ ሜዳዋንም እንደ ይሖዋ የአትክልት ስፍራ ያደርጋል።+

      በእሷም ውስጥ ሐሴትና ታላቅ ደስታ

      እንዲሁም ምስጋናና ደስ የሚያሰኝ መዝሙር ይገኛሉ።+

  • ኢሳይያስ 56:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  7 ቅዱስ ወደሆነው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤+

      በጸሎት ቤቴም ውስጥ እጅግ እንዲደሰቱ አደርጋቸዋለሁ።

      የሚያቀርቧቸውም ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና መሥዋዕቶች በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት ያገኛሉ።

      ቤቴም ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።”+

  • ኢሳይያስ 60:18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 ከዚህ በኋላ በምድርሽ ውስጥ ዓመፅ፣

      ወይም በክልልሽ ውስጥ ጥፋትና ውድመት አይሰማም።+

      ቅጥሮችሽን መዳን፣+ በሮችሽንም ውዳሴ ብለሽ ትጠሪያቸዋለሽ።

  • ኢሳይያስ 65:25
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 25 ተኩላና የበግ ግልገል በአንድነት ይበላሉ፤

      አንበሳ እንደ በሬ ገለባ ይበላል፤+

      የእባብም መብል አፈር ይሆናል።

      በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳትም ሆነ ጥፋት አያደርሱም”+ ይላል ይሖዋ።

  • ሚክያስ 4:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  4 እያንዳንዱም ከወይኑና ከበለስ ዛፉ ሥር ይቀመጣል፤*+

      የሚያስፈራቸውም አይኖርም፤+

      የሠራዊት ጌታ የይሖዋ አፍ ተናግሯልና።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ