ኢሳይያስ
24 እነሆ፣ ይሖዋ ምድሪቱን ወና እና ባድማ ያደርጋታል።+
2 በሁሉም ላይ ተመሳሳይ ነገር ይደርሳል፦
በሕዝቡ ላይ የሚሆነው በካህኑ፣
በአገልጋዩ ላይ የሚሆነው በጌታው፣
በአገልጋይዋ ላይ የሚሆነው በእመቤቷ፣
በገዢው ላይ የሚሆነው በሻጩ፣
በአበዳሪው ላይ የሚሆነው በተበዳሪው፣
በወለድ ተቀባዩ ላይ የሚሆነው በወለድ ከፋዩ ላይ ይደርሳል።+
ፍሬያማዋ ምድር ትራቆታለች፤ ትጠፋለች።
የምድሪቱ ታላላቅ ሰዎች ይዝላሉ።
6 ስለዚህ እርግማኑ ምድሪቱን በላት፤+
በላይዋም የሚኖሩ ሰዎች በደለኞች ሆነው ተገኝተዋል።
የምድሪቱ ነዋሪዎች ቁጥር የመነመነው በዚህ ምክንያት ነው፤
የቀሩት ሰዎችም በጣም ጥቂት ናቸው።+
9 ዘፈን በሌለበት የወይን ጠጅ ይጠጣሉ፤
መጠጡም ለሚጠጡት ሰዎች መራራ ይሆናል።
10 የተተወችው ከተማ ፈራርሳለች፤+
እያንዳንዱ ቤት ማንም እንዳይገባበት ተዘግቷል።
11 በየጎዳናው ላይ የወይን ጠጅ ፍለጋ ይጮኻሉ።
ሐሴት ጨርሶ ጠፍቷል፤
ምድሪቱም ደስታ ርቋታል።+
12 ከተማዋ ፈራርሳለች፤
በሩም ተሰባብሮ የፍርስራሽ ክምር ሆኗል።+
13 የወይራ ዛፍ ሲራገፍ+ እንደሚቀር ፍሬ፣
ወይንም ተሰብስቦ ካበቃ በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ፣+
ሕዝቤም በምድሪቱና በሌሎች ሕዝቦች መካከል እንዲሁ ይሆናል።
14 ድምፃቸውን ከፍ ያደርጋሉ፤
በደስታ እልል ይላሉ።
የሚል ዝማሬ እንሰማለን።
እኔ ግን እንዲህ አልኩ፦ “አቅም አጣሁ፤ አቅም አጣሁ!
ወዮልኝ! ከሃዲዎች ክህደት ፈጽመዋል፤
ከሃዲዎች በማታለል ክህደት ፈጽመዋል።”+
17 አንተ የምድሪቱ ነዋሪ ሆይ፣ ሽብር፣ ጉድጓድና ወጥመድ ይጠብቅሃል።+
18 ከሚያሸብረው ድምፅ የሚሸሽ ሁሉ ጉድጓድ ውስጥ ይወድቃል፤
ከጉድጓዱም የሚወጣ ሁሉ በወጥመዱ ይያዛል።+
የሰማይ የውኃ በሮች ይከፈታሉና፤
የምድርም መሠረቶች ይናወጣሉ።
20 ምድሪቱ እንደሰከረ ሰው ትንገዳገዳለች፤
ነፋስ እንደሚወዘውዘው ጎጆም በነፋስ ወዲያና ወዲህ ትወዛወዛለች።
በደሏም በላይዋ ላይ እጅግ ከብዷል፤+
ዳግመኛም እንደማትነሳ ሆና ትወድቃለች።
21 በዚያን ቀን ይሖዋ በላይ፣ በከፍታ ቦታ ባለው ሠራዊት ላይ፣
እንዲሁም በታች፣ በምድር ባሉት ነገሥታት ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።
22 እነሱም እንደ እስረኞች ጉድጓድ ውስጥ
አንድ ላይ ይታጎራሉ፤
በእስር ቤት ውስጥም ይዘጋባቸዋል፤
ከብዙ ቀናት በኋላ ጉዳያቸው ይታያል።