ምሳሌ
4 በእውቀት አማካኝነት ክፍሎቹ
በተለያዩ ውድ የሆኑና ያማሩ ነገሮች ተሞልተዋል።+
5 ጥበበኛ ሰው ኃያል ነው፤+
ሰውም በእውቀት ኃይሉን ይጨምራል።
7 ለሞኝ ሰው እውነተኛ ጥበብ ሊገኝ የማይችል ነገር ነው፤+
በከተማው በር ላይ አንዳች የሚናገረው ነገር የለውም።
8 መጥፎ ነገር ለማድረግ የሚያሴር ሁሉ
ሴራ በመጠንሰስ የተካነ ተብሎ ይጠራል።+
10 በመከራ ቀን* ተስፋ የምትቆርጥ ከሆነ
ጉልበትህ እጅግ ይዳከማል።
11 ወደ ሞት እየተወሰዱ ያሉትን ታደግ፤
ለእርድ እየተውተረተሩ የሚሄዱትንም አስጥል።+
12 “እኛ ግን ስለዚህ ጉዳይ ምንም አናውቅም” ብትል፣
13 ልጄ ሆይ፣ መልካም ስለሆነ ማር ብላ፤
ከማር እንጀራ የሚገኝ ማር ጣፋጭ ጣዕም አለው።
14 በተመሳሳይም ጥበብ ለአንተ መልካም* እንደሆነ እወቅ።+
ጥበብን ብታገኝ የወደፊት ሕይወትህ የተሳካ ይሆናል፤
ተስፋህም ከንቱ አይሆንም።+
15 በጻድቁ ቤት ላይ በክፋት አትሸምቅ፤
ማረፊያ ቦታውንም አታፍርስበት።
21 ልጄ ሆይ፣ ይሖዋንና ንጉሥን ፍራ።+
ሁለቱም* በእነሱ ላይ የሚያመጡትን ጥፋት ማን ያውቃል?+
23 እነዚህም አባባሎች የጥበበኞች ናቸው፦
በፍርድ ማዳላት ጥሩ አይደለም።+
24 ክፉውን “አንተ ጻድቅ ነህ”+ የሚለውን ሰው ሁሉ
ሕዝቦች ይረግሙታል፤ ብሔራትም ያወግዙታል።
26 ሰዎች በሐቀኝነት መልስ የሚሰጥን ሰው ከንፈር ይስማሉ።*+
27 በደጅ ያለህን ሥራ አሰናዳ፤ በእርሻም ላይ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ አዘጋጅ፤
ከዚያ በኋላ ቤትህን ሥራ።*
28 ምንም መሠረት ሳይኖርህ በባልንጀራህ ላይ አትመሥክር።+
በከንፈሮችህ ሌሎችን አታታል።+